የምግብ ዘይት በመፀዳጃ ቤት ውስጥ ተከማችቶ ተገኘ
MARCH 7, 2022 04:34 PM BY EDITOR
በአዲስ አበባ ከተማ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 03 ያለአግባብ የተከማቸ የምግብ ዘይት በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።
ክ/ከተማው በ11 ሱቆች ላይ ተደረገ ባለው ፍተሻ 442 ሊትር ዘይት በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን አሳውቋል።
ፍተሻ የተደረገው በወቅታዊ የዋጋ ንረት ምክንያት ካሉ 6 ቀጠናዎች በ3ቱ ቀጠናዎች ላይ ብቻ መሆኑ ተጠቁሟል።
ክ/ከተማው በቁጥጥር ስር የዋለው የምግብ ዘይት ባልተገባ ቦታ መፀዳጃ ቤት ውስጥ ተደብቆ መገኘቱን የገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ እንደዚህ አይነት ድርጊት የሚፈፅሙትን “ሌባን ሌባ ” ሲል እንዲያጋልጥ ጥሪ አቀርቧል።
በአግባቡ ስራቸው ላይ የሚገኙ ነጋዴዎች አሁን በያዙት ልክ ዘይትን ወደ ፊት በማምጣት መሸጥ ይኖረባቸዋል የተባለ ሲሆን ህገወጥ ስራዎችን በሚሰሩ ነጋዴዎች ላይ ንግድ ፍቃድ መሰረዝ ጨምሮ ጠበቅ ያሉ እርምጃዎች እንደሚወሰድ ክጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣፍለ ከተማው አስጠንቅቋል። @tikvahethiopia
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ