June 22, 2022

ናዕት (እያመመኝ መጣ ቁ.2)

——————————-

ዘውግ ያወረው ድንበር

መላውን የረሳ

ሳር ያለመልማል ዛሬም

በዕልፍ አዕላፍ እሬሳ

—-

እያረረ ሆዴ ብስቅ

በማሽላ ዘዴ

ና ታደም ይለኛል ደግሞ

በነ ኡ.ኡ . ሬጌ

—-

ብልጭልጭ ቢሆን ዳሱ

ማን ሊታደም ከድግሱ !

—-

ተላላ ዝንጉ ሰብ

የሙታን ሸማ ደዋሪ

ምን አለ አይል ከፊት

ሆኖ ቅርብ አዳሪ

—-

ተናገር አፌ ደፍረህ

ሳትናወጥ ከቶ

ዝም አይሆንም ሜዳ

ተራራ ሞት መጥቶ

—-

ገለል በል ኤሳው

ነፍሴን አንቀህ አታሳሳት

ብታገስ ባሰ ባንተ

የልቤ እሳት

—-

ዶፍ ቢዘንብ እቶን እሳት

ሀገሬን ላልረሳት

ቃል አለኝ ኖሬ

ሞቼም ልክሳት

———///—–

ድንቅ ነው አዳምጡት

https://www.youtube.com/watch?v=1hMVeENjVew