Admin 

Vision Ethiopia _ Amhara massacre

ሰኔ 13፣ 2014 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በቅርቡ ፓርላማ ቀርብው የአማራን ሕዝብ ለማስጨፍጨፍ  የተጀመረውን ዘመቻ ለማስቀጠል ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ፣ በወለጋ አካባቢ በብዙ ሺዎች የሚቆጥሩ አማራዎች እደገና ታርደዋል፤ ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ እንደተለመደው በዱር በገደሉ ተሰደው  እንዲሰቃዩ ተደርገዋል:: 

የአማራው ሕዝብ ሰቆቃ፣ችግርና እልቂት የማይከነክነዉና የማይሰማው፣ ሌላው እስካሁን ያልተነካው  የኢትዮጵያ ክፍል፣ ነገ እጣና ፋንታው የእሱ መሆኑን መረዳት ተስኖት፣ በዘረኛው ስርአት ደንዝዞ፣ ለዚህ  ወንጀለኛ መንግሥት አጎብድዶ ይታያል:: 

በውጭ የሚኖርው የአማራ ወገን፣ያካበተውን ኃይል እና ኃብት አቀናብሮ እና በአንድነት ቆሞ፣ በትውልድ አገሩ እየተካሄደ የሚታየውን የአማራ ዘር-ጥፋት ዘመቻ ለመከላከል ብቃት ጎድሎት፣ የአዞ  እንባ እያነባ፣ በጥቃቅን ጉዳዮች ተለያይቶ፣ ፋይዳ ያለው አስትዋጾዖ ከማድረግ ተቆጥቦ እየዋዥቀ  ይገኛል።  

የዓለም-አቀፍ ሕብረተ-ስብና ተቋማት፣ በተለይም ለፍትህና ለሰው ልጅ መብት ጠበቃዎች ነን ባይ  ምዕራባውያን መንግሥታትና ድርጅቶች፣ በወያኔ ሰበካ ታውረው፣ ወይም በዘረኝንት መርዝ ደንቁረው፣  በአማራው ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን የዘር ጥፋት ዘመቻ ላለማወቅና ላለመስማት “ጆሮ ዳባ ልበስ” ብለው ይታያሉ። 

ይህ አሰቃቂ እልቂት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ መንግሥት ስልጣኑን ከተረከበበት ጥቂት ወራት  ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በአይነቱ፥ በዘዴውና በብዛቱ እየጨመረና እየከፋ የመጣ ነው። አላማው የዐብይ  አሕመድ መንግሥት ታጥቆ የተነሳለትን፣ የኦሮሙማን የበላይነት እቅድ እውን ለማድርግ ስለሆነ፣ያ ግብ  እስከሚረጋገጥ፣ የንጹሃን ደም እንደ ዉሃ ሲፈስ ይቆያል። ዛሬ በወለጋ፣ ቀደም ሲልም በተመሳሳይ  አካባቢዎችና ክልሎች ሲካሄድ የቆየው፣ የዘር ማጥራትና ፍጅት ዘመቻ፣ ነገም፣ ከነገ ወዲያም  ይቀጥላል! 

የተራቀቀው እቅድ በሥራ እየተከናወነ ያለው፣ እንደ ሩዋንዳው መቶ ሺዎችን በአንድ ጊዜ በማረድ  ሳይሆን፣ አሁን እንደሚታየው፣ ጊዜ ወስዶ እያዘናጉ፣ በተደጋጋሚ በመቶዎች የሚቆጠሩትን በመፍጀትና  በሺዎች የሚገመቱትን ከቀዬዎቻቸው በማባረር ሆኖ ይታያል

Page | 1 

ታዲያ ትልቁ ጥያቄ፣ “የዐብይን መንግሥት ለመኮነን ሀቀኛ ኢትዮዽያውንና ምእራባውያን መንግሥታትና  ተቋማት ምን ያህል ተጨማሪ የአማራ ደም እስከሚፈስ ይጠብቃሉ?” የሚለው ነው። 

ቪዥን ኢትዮጵያ (ራዕይ ለኢትዮጵያ)፣ በአማራው ሕዝብ ላይ፣ በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ  መንግሥት እውቅና፣ እየተከሰቱ ያሉትን አስከፊ የግፍና የበደል እርምጃዎችን አጥብቆ እያወገዝ፣  ኢትዮዽያዊያንና ምእራባውያን መንግሥታትና ተቋማትም የታሪክ ተወቃሽ እንዳይሆኑ፣ በግፍ  ከሚሰቃየው የአማራው ተጠቂ ወገን እንዲቆሙ ይጠይቃል። በተለይም፤ 

1. ፍትህ ወዳዱ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ለዚህ በብዙ ሺህ ለሚገመት ንጹሃን ሕይወት መቀጠፍና በብዙ  ሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ስዎች መፈናቀል፣ የዐብይ አሕመድ መንግሥትን በቀጥታ ተጠያቂ  እንዲያደርግና፣ወደፊትም በተለያዩ አካባቢዎች በሚኖረው አማራ ላይ አደጋ እንዳይደርሰ  የሚያስፍለገውን መስዋእትነት ከፍሎ ለመከላከል በቁርጠኝነት እንዲታገል፤ 

2. በውጭ የሚኖርው የአማራ ወገን፣ አገር ዉስጥ በኦሮሞ ጽንፈኞች የሚካሂደውን እልቂት ለማስቆም ኢላማ ባደረገ መርሃ ግብር ስር ተራጅቶ፣በአንድነት በመቆም፣በተቀነባበረ መንገድ የውስጥና የዉጪ ትግል እንዲያካሂድ፤ 

3. የውጭ ዜና አገልግሎቶች፣ በአማራው ሕዝብ ላይ በወያኔና በኦሮሙማው መንግሥት እስከዛሬ  ድረስ የተፈፀሙትን እልቀ-መሳፍርት የሌላችውን ግፎችና ጭፍጨፋዎችን አይተው እንዳላዩ  ሲያሳልፉ ቢቆዩም፣ ከእንግዲህ ይህ ዓለም-አቀፋዊ ዝምታቸዉን ሰብረው የአማራውን  እልቂት፣ሰደትና መከራ በማያሻማ መንገድ በማስታወቅና በመመዘገብ የተጣለባቸዉን ሃላፊነት  እንዲወጡ፤  

4. በስልጣን ላይ ያለው የአሜሪካ አስተዳደርና ሌሎችም ምእራባውያን አገሮች፣የዩክሬይንን ሕዝብ  ለመርዳት እንደተረባረቡት ሁሉ፣በዐብይ አሕመድ አስተዳደር ላይ አስፈላጊዉን ማእቀብ  በመጣል፣ በአማራው ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማስቆም እንዲጥሩ፤ 

5. በመጨረሻም፣የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ሌሎችም የዚህ መግለጫ ግልባጭ የሚደርሳቸው  የሰብዓዊ መብት ጠባቂ ድርጅቶች፣ ለወያኔ ሽንጣቸውን ገትረው በታገሉበት መጠን፣ አሁንም የአማራዉንም ሰቆቃ ተገንዝበው የሚጠበቅባቸዉን ድጋፍ እንዲሰጡ እንጠይቃለን።  

የ ቪዝን ኢትዮጵያ (ራዕይ ለኢትዮጵያ) ቦርድ

__