· የርዋንዳ ቱትሲ ጀኖሳይድ
ከኢትዮጵያ አማራ ጀኖሳይድ
===============
የሩዋዳ የዘርፍጅት ከመጀመሩ በፊት ከቅድመ ሁኔታወች አንዱ እና እስከ ፍጅቱ ጅማሮ ዋና ሆኖ የቀጠሉ የፕረስ እና የሬዲዮ ሚዲያወች ነበሩ። በ 1990 በካንጉራ ጋዜጣ ቱትሲወችን በካርቱን ምስል እና በተለያየ ግራፊክ ፎቶ ጭራቅ አርጎ ማውጣት ተጀመረ። ይህ ሕዝብን ደም መጣጭ ምስል አድርጎ የመሳሉ የዘር ጥላቻ እየተለመደ እና እውነት ነው እየተባለ ሄዶ በ 1993 እ ኤ አ Radio-Television Libre des Mille Collines (RTLMC) የተባለ ሬዲዮ ጣቢያ በሁቱ ደጋፊ እና በስልጣን ላይ በነበረው መንግስት የሚደገፍ ተጀመረ። ይህ ሬዲዮ ጣቢያ ቤት ውስጥ እንኳን ሊነገር የሚከብድን የጎዳና (ዱርየ) ቋንቋ በመጠቀም የጥላቻውን ፕሮፖጋንዳ አብዝቶ እና አክርሮ ቀጠለበት።
በዚህ ሬዲዮ ጣቢያ ጸረ ቱትሲ ቀልድ፣ ዝና ያላቸው ሙዚቃወችን የሙዚቃው መቅረብ ወጣቱን ለመሳብ እና አዳማጭ እንዲሆን በስልት የተሰራ ሲሆን ሌላው ፕሮግራም ተይዞለት ሰካራም የመሰለ ሰው የሚያቀርባቸው ከዚህም ከዚያም የሚረግጡ ግን በእርግጥም ጸረ ቱትሲ ጥላቻን የሚያራግቡ አዳማጭ እንዲሆኑ የታሰቡት ደግሞ የቀን ሰራተኞች፣ ዱርየ ኪስ አውላቂወች እና መንደር እና ከተማ ሲለቃቅሙ የሚውሉት እንዲሆኑ በመታሰብ የተደረገ ዘዴ ነበር። ይህ የተቀናበረ የሬዲዮኑ ስርጭት እና ፕሮግራሞች በግዜው በነበረው የብዙሀኑ ሁቱ የሚባሉ ዝርያወች መንግስት ሲሆን ለመብት አምጾ የነበረውን ቱትሲ ዘመም የሆነን አማጺ በህዝቡ ጉዳት ለማድረስ የተዘየደ መላ ነበር። እናም መንግስታዊ ድጋፉ የተቸረው በመሆኑ የጸረ ቱትሲው የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ግቡን መታ።
ሬዲዮ ጣቢያውን እና የጥላቻ መሳሪያ የነበረውን ጋዜጣ ለማዘጋት ቀድሞ አደጋውን ያዩት የቤልጂያን ኤምባሲ የምእራብ ዲፕሎማቶችን መማጸን ቢጀምሩም በተለይ የአሜሪካ ኤምባሲ Freedom of speech መብት ነው በሚለው መርህ በመመርኮዝ ድጋፍ ሳይሰጥ ቀረ። ሌሎችም የአውሮፓ ሀገራት ዲፕሎማቶች ጉዳዩ የግል ነጻነት ጋር በማቆራኘት ቸልታን መረጡ። የአሜሪካ አምባሳደር ዴቪድ ሮውሰን David Rawson, the US ambassador, said that its euphemisms were open to interpretation. The US, he said, believed in freedom of speech. በሚል ጉዳዩን በቸልታ ብቻ ሳይሆን መርህ እንዳይጣስ በሚያስመስል የቤልጀምን አንባሳደር ሀሳብ በአጭር አስቀረው። ብዙ እሩዋንዳውያን የጥላቻው አካሄድ ያሳሰባቸው ጉዳዩን በሚዲያ አንስተው ሁሉም በሚባል ታሰሩ ወይንም መዳረሻቸው ጠፋ። ከዚህ በኋላ አደጋው ከዚህ በኋላ የርዋንዳ የጅምላ ፍጅት አይቀሬ ሆነ አይቀሬነቱን እያወቁም ይሁን በቸልታ ምእራባውያን ይሁንታን ያሳፈሩበት ፍጅት በአፍሪካውያን ላይ ተፈጸመ።
ከፍጅቱ በስተጀርባ እና ለፍጅቱ የገንዘብ እና የፕሮፖጋንዳ ወጭ ሸፋኝ የነበሩት የሰሜን እርዋንዳ ባለሀብቶች እና የመንግስት ደህንነቶች ነበሩ። ለፍጅቱ መንገድ አስተካካይ፣ ቤንዚን አርከፍካፊ የነበረው ሬዲዮ በሚከፈላቸው የፍጅት ምሁራን የተካሄደ ነው። ምሁር ሲባል አዋቂ ተመራማሪ ማልት ግን አይደለም ። የልቅ ስጋ ለብሰው ቁመው የሚሄዱ አጋንንቶች ማለት የተሻለ ትርጉም ይሰጠዋል።
ሰሞኑን የተፈጸመው ወንጀል እና እስካሁንም መቀጠሉ የሚነገርለት የምእራብ ወለጋ ፍጅት ሰሞኑን የተጀመረ አይደለም። ለአመታት የቀጠለ ነው። አስገራሚ የሚሆነው እና ከርዋንዳ ፍጅት የሚያመሳስለው በሀገሪቱ ሰፊ ቁጥር ያለው ጎሳ ስልጣን ላይ መሆኑ እና ግድያው ያለማቋረጥ ከቦታ ቦታ መቀጠሉ ነው።
ይህ መጠነ ሰፊ የግንቢ ፍጅት ልዩ የሚያደርገው ሕጻናት እናቴ እናቴ እያሉ እየጮሁ የፍጅቱ ተጠቂ መሆናቸው ገዳዮች ቆመው የሚሄዱ ስጋ ለባሽ ሰወች ሳይሆኑ አጋንንት መሆናቸው የሚያሳይ ምልክት ነው። ሰወች የተለያየ ምክንያት ሊሰጡ ይችላሉ እኔ እንደግለሰብ ያየሁት የሰማሁትን ግን ለትምህርት ይሆን ዘንድ ላጋራ እፈልጋለሁ።
ለምሳሌ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ፓርላማ ቀርበው የተናገሩት ንግግር አንድ ስልጣን ላይ ያለ ሰው ሊናገረው የማይገባ ነው ብየ አምናለሁ። የዘር ፖለቲካ አጡዘው ጫፍ ያደረሱ የዘር ፖለቲካ መሪ እንደመሆናቸው፤ ወይንም የዘር ፖለቲካ ከሮ አሁንም ስልጣን ላይ ወጥተው የተበዳይ ስሜትን – ወይንም ማረጋገጫ የለሽ ተበዳይነትን በአንድ ፓርላማ በገለጹበት መልክ ያውም የደም ብስጭት በተሞላበት ኃይለ ቃል ለተጠየቁት ጥያቄ መልስ የሰጡት ከጣሊያን ወረራ ግዜ ጀምሮ በዳይ ተብሎ የተፈረጀ የአማራ ሕዝብን ተወካይ ለሆነ የፓርላማ አባል ሲሆን- ይህን የሚያይም የሚሰማም የሳቸው ዘር ተካፋይ እርሳቸው የተበሳጩበትን በእጥፍ ሊበሳጭ እንደሚችል እና ወደብቀላ ሊሄድ እንደሚችል መታወቅ አለበት።
ወደ መነሻ ታሪኬ ልመለስ እና ስለ ርዋንዳ ጀኖሳይድ እና ለ 900,000 ቱትሲወች እልቂት ክብሪት ጫሪ የሆነችዋን ሁኔታ ላሳይ። ግድያው ከመጀመሩ ሰአታት በፊት የ Radio-Television Libre des Mille Collines (RTLMC) የርዋንዳ ፕሬዚዳንት የተሳፈሩባት አውሮፕላን ተመትታ ሁቱው ፕሬዚዳን መሞታቸውን እና ያለምንም ጥርጥር ገዳያቸው ቱትሲ አማጽያን ናቸው ብሎ ሬዲዮኑ ማወጁ በቀጣይ ይህን ግድያ ተከትሎ ሁቱወችን ወደስራ እንዲሰማሩ ትእዛዝ መስጠት የግድያው መጀመር ዋና ሆነ። ግድያው እየተካሄደ ከነበሩ መፈክሮች አንዱ “የመቃብሮች ጉድጓድ ገና አልሞላም” (The graves are not yet full) የሚል የሬዶዮኑ መፈክር ተደጋግሞ ይሰማ ነበር።
እንዲህ የሚል አባባል አለ “ሁለት ጓደኞች መንገድ ወጥተው ሲመሽባቸው አንድ ቦታ ተጠለሉ እና ተኙ፤ ከዚያ አንደኛው የሚቀሰቅስ ድምጽ ሰምቶ ጓደኛውን ምንድነው የምሰማው ሲለው ዝም በል ጅብ የኔን እግር እየበላ ነው” አለ ይባላል። ዛሬ ሐገራችን በጣም አሳሳቢ ደረጃ ከደረሰች አመታት አስቆጥረዋል። በገዥወች የሰው ህይወት በጅምላ ፍጅት ጠፍቶ የሐዘን መግለጫ – ከመስጠት – ሕዝብን ስለአደጋው አሳሳቢነት ከመምከር እና አደጋውን ለማቆም የሚሆነውን ሁሉ ከመክፈል – ይልቅ በቴሌቪዥን መስኮት አይተን የታዘብነው በፓርላማ የአደጋውን ግዝፈት ለማሳሰብ የተነሳውን የፓርላማ አባል ማይክራፎን እስከ መዝጋት እና ማንገራጠጥ የተሄደበት ምስል ለፍጅቱ ፈጻሚወች ድጋፍ መስጠት ካልሆነ ምን ሊሆን ይችላል? ሌላው በዚሁ ሰሞን በተከፈተ የፓርላማው መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስቴርን ያክል ሰው በፓርላማ ፊት ቅርቦ “በደላችንን ይቅር ብለን ነው እንጅ” እሰከማለት መድረስ እና የአንድ ተበዳይ ወገን ደጋፊ ሆኖ መገኘት ያውም በተረት ተረት አውሮፓውያን በፈጠሩት ተረት መሪው ሲናገሩ ከማየት ሌላ ምን ልንጠብቅ እንችላለን?
በበኩሌ ይህን ስጽፍ ለማሳየት የፈለግሁት የአደጋው አነሳስ እጅግ ዘግናኝ እንደመሆኑ እና ኋላስ ሊቆም ወደማይችልበት ቢዘልቅ እና የዘር ከዘር ፍጅትን ቢያስከትል ማን ሊሆ ን ነው ተጠያቂ? የዘር ፖለቲካን እንደ ጥሩ ስርአት ለነሱ እስከተመቸ ያስቀጠሉት የዘር ሹሞች – ህግ እና ደቡን ታቅፈው አሁንም የድላችን ውጤት ነው የሚሉት እና ሁሌ ደማቸው በፈላ ቁጥር የሚያሳዩት ባህርይ ቀጣይ አደጋው ብዙ መሆኑን እንዲገነዘቡ ቢሆን እና አደብ ቢገዙ፤ መሰረት የለሽ ቂም እና በቀልን ከነሱ አዕምሮ አውጥተው ሕዝባቸውን ቢያስተምሩ የተሻለ ዜጋን፣ ሰላም ያላት ሀገርን ለመስጠት Pioneers በሆኑ እና ታሪክ ሲያወድሳቸው በኖረ። ያሳይሆን ስለቀረ እና የዘር ፍጅቱ እየበረደ ሳይሆን እየሰፋ በመሆኑ ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን አደጋ በኔ አልደረሰም ብሎ ዝምታን ከመምረጡ ወጥቶ ወይንም ዘረኞችን ወርቅ እያስጠለቁ የሌላቸውን እየቀቡ ማሽሞንሞን መጨረሻው የቋያ እሳትን እንደማዳፈን መሆኑን መረዳት እና ከነአካቴው የዘር ፖለቲካ መራሹን ህግ ለማስወገድ በቁርጥ መነሳት ለመጭ ትውልዶች ለልጅ ለልጅልጆች መከራን ከማውረስ (ዛሬን ከተሻገርን ማለት ነው) ዛሬ መስዋ’እት ከፍሎ የሐገርን ክብር እና ስልጡን ፖለቲካን መገንባት ይገባል/ይቻላልም።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ፤ ያስባትም!
Ethiopia Shall Prevail!!!
17172 SharesLikeCommentShare