August 18, 2022

12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት 12ኛ ክልል እንዲቋቋም የሚያስችል ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ወስኗል።

ምክር ቤቱ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ስር የነበሩ 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል እንዲደራጁ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተቀብሎ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ወስኗል።

ሕዝበ ውሳኔ የሚያካሂዱት ፦
– የወላይታ ዞን፣
– የጋሞ ዞን፣
– የጎፋ ዞን፣
– የደቡብ ኦሞ ዞን፣
– የጌዴኦ ዞን፣
– የኮንሶ ዞን፣ እንዲሁም
– የደራሼ ልዩ ወረዳ፣
– የአማሮ ልዩ ወረዳ፣
– የቡርጂ ልዩ ወረዳ፣
– የአኧ ልዩ ወረዳ እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ናቸው።

ቀሪዎቹ የሀድያ ዞን ፣ ሀላባ ዞን ፣ ከንባታ ጠንባሮ ዞን፣ ጉራጌ ዞን ፣ ስልጤ ዞን እና የም ልዩ ወረዳ በነባሩ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይቀጥላሉ መባሉን አሚኮ ዘግቧል።