
ሁለት ነገሮችን ግልጽ ስለማድረግ!
1. እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት የቆቦ ከተማና አካባቢው እስከ አሁኗ ስአት ድረስ በጠላት ቁጥጥር ስር ነው የሚገኘው። አንዳንድ ወገኖችና የማህበራዊ ሚዲያ ሰዎች የወገን ጦር ቆቦ ገብቷል በማለት የሚሰጡት መረጃ ትክክል አይደለም። ይህም ሆኖ የወገን ጦር በቆቦና አካባቢው እየወሰደው ባለው የተቀናጀ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ አማካኝነት ቆቦ ከተማ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ነጻ ሊወጣ እንደሚችል ይታመናል።
–
2. “በቆቦ ከተማ ይገኙ የነበሩ 60,000 የትግራይ ተፈናቃዮች ከትህነግ ታጣቂዎች ጋር በመተባበር የቆቦ ከተማን ሕዝብ እያስጠቁ ነው” እየተባለ የሚለቀቀው መረጃም ውሸት ነው። ሁኔታቸው ተጣርቶ ወደ መጠለያ ጣቢያ እስኪላኩ ድረስ ቆቦ ከተማ ውስጥ የሚቆዩት የትግራይ ተፈናቃዮች ቁጥር በአጠቃላይ ከአንድ ሽህ በታች እንደነበረ ይታወቃል።
–
ከእነዚህ ውስጥ በቡድንና በግለሰብ ደረጃ ሆነው ጥቆማ እየሰጡ በግለሰቦች ላይ ጉዳት እንዲደርስ እያደረጉ የሚገኙ እንዳሉ መረጃ ደርሶኛል። በእነዚህና በሌሎችም አስጠቂ ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ ጥብቅ ክትትል አድርጎ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ የአካባቢው ሕዝብ ሀላፊነት ነው።
ከዚህ ውጭ የትግራይ ተፈናቃዮች የሚገኙት ሐይቅ ከተማ አጠገብ በሚገኘው ጃሪ መጠለያ ጣቢያ ሲሆን ቁጥራቸውም ከላይ የተባለውን ያህል አይሆንም። ወደዚህ መጠለያ ጣቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ራዮችም በስህተት ከትግራይ ተወላጆች ጋር አብረው እንዲገቡ በመደረጉ ወገኖቻቸው ወደሚገኙበት ጃራ መጠለያ መግባት ይሻሉና ይህም እውነታ ሊታወቅ ይገባል።
–
ይኸ መጠለያ ቦታ ደግሞ ከቆቦ ከተማ 140 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው የሚገኘው። እናም መረጃዎች ትንሽ እውነትን በመያዝ በተጋነነ መልኩ ቢቀርቡ እኮ ምንም አልነበረም፣ እንዲሁ ከሜዳ ተነስቶ መቀደድ ግን የጤና አይደለም። ራስን ትዝብት ከቶ ተዓማኒነትንም ያሳጣልና ቢታሰብበት መልካም ይመስለኛል።
