·

“ያዳፈኑትን ታሪክ እኛ እንግለጠው …”

******

የአማርኛ መገኛ …በሆነችው በታሪካዊቷ አምሃራ ሳይንት የምትገኘው ጥንታዊቷ ርዕሰ አድባራት ወ ገዳማት ተድባበ ማርያም ብቻ ያለውን የታሪክ ልዕልና እወቅና ተደመም…

→ ከተመሰረተች 2996 ዓመታት አስቆጥራለች። ከክርስቶስ

ልደት በፊት ከቀዳማዊ ምኒልክ ጋር ከእስራኤል

በመጡት ሌዋውያን ተተከለች።

→ በአመሰራረቷ ከአክሱም ጽዮን እኩል የኦሪት መስዋዕት

ይቀርብባት ነበር ፣

→ ከቀዳማዊ ምኒልክ እስከ አፄ ኃይለ ሥላሴ ድረስ በቅብዓ

ነገሥት ከብረው ለነገሡ ደጋግ ነገሥታት ኃይለ

እግዚአብሔር የሚያገኙባቸው ጥንታዊያን ቅዱሳት

መካናት ከሆኑት ከ፬ቱ ጥንታዊያን መናብርተ ጽዮን

መካከል አንዷ ናት።

→ በውስጧ ጠብቃ በያዘችው ቅርስ የሚተካከላት የለም፣

→ ደገኛው ንጉሥ አጼ ገላውዴዎስ ሀገር እና ቤተክርሲቲያንን

በግራኝ ከመውደም ለማዳን ሲዘምት ማዕከሉን

ከአምሐራ ሳይንት አድርጎ የተድባበ ማርያምን ታቦተ

ልደታ ይዞ ዘምቶ ነበር ድሉን ያወጀው።

→ እንደ ገነት ፲፪ መግቢያና መውጫ በሮች ያሏት ሲሆን

እነርሱም፦ ፊት በር፣ የጌላት በር፣ የታንኳ በር፣ አምጣ

ፈረሴን በር፣ ግራዢ በር፣ ገተም በር፣ አቅቻ በር፣ ፈረስ

መጣያ በር፣ ቦካ በር፣ ጨረር በር፣ የጎድ በር እና

መርገጫ በር ይባላሉ።

የአካባቢው ሕዝበ ክርስቲያንም በሚደንቅ መተባበር በነዚህ በሮቿ ሁሉ በየተራ ታጥቆ በንቃት የሚጠብቃት አስገራሚ ገዳም ናት።

→ የእመቤታችን እናት የቅድስት ሀና የራሷ ፀጉር፣ የ፳፰

ሰማእታትና የ፮ እጨጌዎች ዐጽማቸው በክብር ያረፈባት

ቅድስት ቦታ ናት።

→ በግእዝ፣ በአረማይክና በአረብኛ ቋንቋዎች የተጻፉ

በወርቅና በብር የተለበጡ እጅግ በርካታ ጥንታዊ ቅዱሳት

መጻሕፍትን ለዘመናት ጠብቃ ያቆየች መካነ ቅርስ ናት።

→የአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን፣ የአቡነ ፊልሞና እና

የሌሎችንም ቅዱሳን የእጅ መስቀሎች፤ በብር በወርቅና

በአልማዝ ፈርጥ የተሰሩ የቀደሙ አበው ካባዎችንና

ዘውዶችን የያዘ ቤተ መዘክር ያላት አስደናቂ የታሪክ

ማሕደር ናት።

→ የብፁእ አቡነ ጌርሎስ መንበር፣ የአንጋፋዎቹ የድጓ

ሊቃውንት የአዛዥ ጌራና የአዛዥ ዘራጉኤል፣ የዋድላ ቅኔ

መስራች ሊቅ የዮሐንስ ገብላዊ ቅኔ የተፈጠረባት ናት።

→ በአላውያንና መናፍቃን ነገሥታት ዮዲት ጉዲት፣ ግራኝ

አህመድ፣ አፄ ሱስንዮስ፣ በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ወቅት

ሁሉ የእሳት ቃጠሎም ሆነ ውድመት ሳያገኛት አልፋ

ከነሙሉ ክብሯ ያለች እና በርካታ ቅርሶችንም ከወረራው

አትርፋ ከጠላት ጠብቃ ያቆየች የታሪክም የእምነትም

የባህልም ባለአደራ ናት።

→ ወንጌላዊው ቅ/ሉቃስ የሳላት ባለ፫ ተከፋች የገበታ ሥዕለ

አድኅኖ ያለችበት የጥንታዊያት ስነጥበባዊ ቅርሶች መገኛ

ናት።

→ ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ ከቀዳማዊ ምኒልክ

ጋር ከመጡት 300 ሌዋውያንና 12000 በኩራት

መካከል በሊቀካህናቱ አዛርያስ ፈቃድ ከ12ቱም ነገድ

ተውጣጥተው በቦታዋ ላይ ሰፍረው በኖሩት 2,500

እስራኤላውያን በዕብራይስጥ ቋንቋ የተሰየሙና የቦታዋን

ታሪክ ምጡቅነት የአገራችንንም ልዕልናና ምስጢራዊነት

የሚገልጹ ከ18 በላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቦታዎች

በተድባበና አካባቢዋ ዛሬም ታሪካዊ ስያሜያቸውን

እንደያዙ ይገኛሉ።

→ በአማራ ሳይንት ተድባበ ማርያም ርዕሰ አድባራት ወ

ገዳማት እነማን አገለገሉ …

ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን፣

አቡነ ፊልሞና፣ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ፣ አቡነ ዜና ማርቆስ፣

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ አባ ጽጌ ድንግል፣ ፱ቱ ቅዱሳን፣

በአቡነ ኢየሱስ ሞዓ ቡራኬ ከተላኩት 800ው ንቡራነ እድ

ቁጥራቸውና ስማቸው ያልተገለጠ በርካታ ቅዱሳን

ያገለገሉባት ጥንታዊት መካነ ጸሎት ናት።

የቅዱስ ያሬድ ድጓ የተመለከተው – አምሃራ ሳይንት

ዮሐንስ ገብላዊ ቅኔውን የደረሰው – አምሃራ ሳይንት

አባ ጽጌ ድንግል ማህሌተ ጽጌን የደረሱት – አምሃራ ሳይንት

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ -ሰዓታቱን የደረሱት- አምሃራ ሳይንት

አርጋኖን የተደረሰው – አምሃራ ሳይንት

መጽሐፈ ምስጢር የተደረሰው – አምሃራ ሳይንት

አጼ በዕደ ማርያም ቅኔ የተማሩበት – አምሃራ ሳይንት

አፄ ገላውዲዮስ ማዕከላቸው የነበረው – አምሃራ ሳይንት

ድጓ ክርስቶስ ተአምራት በሰራባቸው የእሁድ እለታት ተከፍሎ የተመለከተው

በአምሃራ ሳይንት

እነዚህ ሁሉ ሐብታት የተገኙበት የሐይማኖት አገር የታሪክ ማማ እንዴት ለምን ታሪኩ ተዳፈነ ?

አምሃራ ሳይንት ጥንታዊ ስሙን ሙጥኝ ብሎ ሳይለቅ መኖሩ አምሃራ ጠላት ነው ይጥፋ ለሚሉ ሁሉ ተጋልጦ ቆይቷል። አምሃራ ጠላት ነው ይጥፋ ያሉ ሁሉ ከምንጩ ይድረቅ ብለው ሲያዳፍኑት ኑረዋል።

***********

***********

ግንቦት 1 ቀን እግሮች ሁሉ ወደ ታሪክ ምንጭ ወደ አምሃራ ሳይንት ወደ ተድባበ ማርያም ያቀናሉ።

……………