· Benta Sina  

· ስለኤፍራጥስ_ወንዝ_መድረቅ_መጽሐፍ_ቅዱስ_ምን_ይላል? መድረቁስ ምኑን ያመለክታል?=======================

ኤፍራጥስ ወንዝ መነሻው ከምስራቅ ቱርክ አድርጎ ከሶሪያ ወደ ኢራቅ በማለፍ ከጤግሮስ ወንዝ ጋር በመዋሃድ ሁለቱንም የሻት አል-አረብ ወንዝን ይፈጥራል፣ ይህም ወደ ፋርስ ባህረ ሰላጤ እስኪፈስ ድረስ ጉዞውን ይቀጥላል።

ይህ ወንዝ በመካከለኛው ምስራቅ ረዠሙና ትልቁ ወንዝ ሲሆን ርዝመቱ 2,800 km፣ የምንጭ ከፍታ ደግሞ 4,500 m አማካይ ይሆናል።

ወንዙ እንደደረቀ አለም አቀፍ ሚድያዎች ሰሞኑ እንደዘገቡ ይታወቃል።

ስለኤፍራጥስ ወንዝ በመጽሐፍ ቅዱስ

=======================

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለኤፍራጥስ ወንዝ ከ23 ጊዜ በላይ የተጠቀሰ ሲሆን በመጀመሪያ የተጠቀሰው ኦሪት ዘፍጥረት 2: 15 ላይ ከአራት ወንዞች አንዱ እንደሆነ። መጽሐፍ ቅዱሳችንም ኤፍራጥስ ወንዝ ትልቅ ወንዝ እንደሆነ ብዙ ቦታ ተጽፎ እናገኛለን።

ለአብነት ዘፍ 15፣ ኦሪት ዘዳግም 11: 24።

ከዚህ በጨማሪ በአዲስ ክዳን ውስጥ (የዮሐንስ ራእይ 9 ፡14)

=====================

በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩ አራት ገዳይ መላእክት እንዳሉና በመጨረሻው ዘመን እንደምፈቱ ተጽፎዋል።

ስፈቱም ሰዎችን 1/3 እንደምገድሉ በዮሐንስ ራእይ 9 ፡15ላይ ተፅፎ እናገኛለን። የ

እግዚአብሔር ቃል እውነት ነው።

(የዮሐንስ ራእይ 9 ፡14-21 አንብቡ)

=====================

14፤ መለከትም ያለውን ስድስተኛውን መልአክ። በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው አለው።

ስለወንዙ መድረቅና ለምን እንደምደርቅ(የዮሐንስ ራእይ 16 )

=====================

12፤ ስድስተኛውም ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውኃው ደረቀ።

ወንዙ መድረቁ ምኑን ያመለክታል?

======================

1.የአለም መጨረሻ እየደረሰ እንደሆነ አመላካች ነው።

2. የታሰሩ 4 ገዳይ መላዕክት ከተፈቱ ምድራችን አዳድስ ክስተቶችን ምናልባት ልታስተናግድ ይሆናል።ለምሳሌ ወደ አርማጌዶን ጦርነት ነገሥታትን ያመራሉ። ራዕይ 16:16

3.መቅሰፍቶች በምድርቷ ላይ ይከሰታሉ።

ራዕ 9:18 (ከአፋቸውም በወጡት በእሳቱና በጢሱ በዲኑም በእነዚህ ሦስት መቅሰፍቶች የሰዎቹ ሲሶ ተገደለ።)

የዮሐንስ ራእይ 16 ፡6 ላይ የተፃፈው ቃል ከአሁን በኋላ ትንቢት ሳይሆን እውነት ነው።

እኛስ እንደ ክርስትያን ምን እናድርግ?

=======================

1.ንስሃ እንግባ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ።

2.ተዘጋጅተን እንኑርዘመኑ መጨረሻ መሆኑን አውቀን የጌታን መምጣት ነቅተን እንጠብቅ።

“፤ ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ። ” (የማቴዎስ ወንጌል 24: 42)”፤ እነሆ፥ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ እፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።

” (የዮሐንስ ራእይ 16: 15) ኢየሱስ ክርስቶስ ይመጣል።