·
Belay Bekele Weya · ለ “አባ” ለአባማ “አባ ጨጓሬ”ም አባ ነው
(በላይ በቀለ ወያ)
..ሳያዩ የሚያምኑን ፣ አይተህ ተጠራጠር
ተአምር አየሁ አትበል
ጋንን ያህል ነገር ፣ ሲደገፍ በጠጠር
ይልቅ ተአምር ስራ
ከሚታይ መልስ ላይ ፣ጥያቄ በመፍጠር።
ሁሉንም አትመን ፣ ግን ሁሉን ተጠንቀቅ
ቤትህ በሰማይ ነው
ብሎ ለሰበከህ ፣ ምድርህን አትልቀቅ።
ከስጋ ፍላጎት
አርቀህ ስቀለው ፣ የነፍስያህን ልክ
የቄስ ቃል ስታምን ፣ ቄሱን ግን አታምልክ።
ሁሉ ካህን አይደል
አስሮ የሚፈታ ፣ እየፈታ ሚያስር
ስንቶች በካህን ለምድ
እባብ ደብቀዋል፣ ከጥምጣማቸው ስር።