
በዐዲስ አገር አላሚዎች የገጠማት ፈተና ምንድነው?…
ቤተ-ክርስቲያን በእነዚህ ዘመናት ሁሉ የኢትዮጵያ አዕማድ በመሆን ግዙፍ ማኀበራዊ ተቋምነቷን ያስመሰከረች አምሳለ-ሀገር ነች፡፡
በርግጥ፣ ይህ የአጥፍቶ የመጥፋት ጉዞ፣ በእነሱ የፖለቲካ ስሌት ዐዲስ አገር የማበጀቱ ቁልፍ አካል ተደርጓል።
[ተመክሮም ተዘክሮም የማይታረመው] የዐቢይ አህመድ አውዳሚ መንገድ…
ሰሞኑን ደግሞ፣ በዚሁ በሚታወቅበት ፍርደ-ገምድልነቱ፣ የአገር ምስረታ ቅዥት ማስፈፀሚያ የሆነውን የተወገዘ ቡድን፣ የቅዱስ ሲኖዶሱ አቻ አድርጎታል።
በግልፅ ዐማርኛ፣ እውነተኛውን የቤተ-ክርስቲያናችንን ጥያቄ፣ ‘የፖለቲካ ነጋዴዎች’ እንዳይጠልፉት በብርቱ እንጠንቀቅ!!
(በዚህ አጋጣሚ፣ የቤተ-ክርስቲያን ፈተና አሳስቧቸው አጋርነታቸውን ያሳዩ የሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች ምስጋና ይገባችኋል!)
መንግሥት ሆይ፣ የረከሰ እጅህን ከቤተ-ክርስቲያኒቷ ላይ ታነሳ ዘንድ በጨዋ ቋንቋ ትጠየቃል!!!
እናት ቤተክርስቲያን ከፊቴ ቅደም ባለችኝ ቦታ ሁሉ ለመገኘት እኔ ልጇ ወልደሰማይት በቃሌ እቆማለሁ!!
