በአየር ንብረት ለውጥ እና በግጭት ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለችግር በመጋለጣቸው እርዳታን እንደሚሹ እየተነገረ ነው። በዚህም ሳቢያ በአገሪቱ ውስጥ ከ20 ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ የሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልገው የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ኦቻ) ገልጿል። የአገር ውስጥ፣ ዓለም አቀፍ እና የግለሰቦች ስብስብም ለችግር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ለመርዳት …