ዓድዋ ላይ የተሸነፈው ጠላት መርዘኛ ትርክቱ ግን ዛሬም ኢትዮጵያን እያሰቃያት ነው . . . /
ዮናታን ተስፋዬ

የቅኝ ግዛት አንዱ ስልት የአንድን ማህበረሰብ ምልክቶች ማጥፋት ነው… symbolic representations, including unifying historical figures. Destroying icons is one thing, making them subjects of division is a whole other level of colonial rule.
እጅግ የሚኮሰኩሰውና የሚከፋው ግን የገዛ ወገን በጠላት ስልት ራሱን ከውስጥ እየበላ ተከፋፍሎና ተዳክሞ ለመጥፋት (not necessarily physically) የገዛ ታሪካዊ ምልክቶቹንና የአንድነቱን ተምሳሌቶች እያራከሰና እያደበዘዘ መመልከቱ ነው።
ማደብዘዝ ማራከስም አልበቃ ብሎ ይህ የትርክት መዛባትና መዘዙ የገባቸው፤ የታሪክ እና historical figures ምልክትነት ፋይዳ የተረዱ፤ ነፃነት ተጠብቆ የቆየበትን የድል በዓል የድሉ አውራ ንጉሥ ሐውልት ስር ተሰባስበው በነፃነት ለማክበር ተቸግረው እንግልት ሲደርስባቸው መመልከት ያሳፍራል…
ቅኝ ገዢ ጠላት ዓድዋ ላይ ድል ቢደረግም፤ የጠላት መርዘኛ ሀሳብ ግን ላለፉት 30 ዓመታት ስርዓት ተበጅቶለት የሀገራችንን ክብር በገዛ ወገኖቻችን ማዋረዱ ዛሬም ያበቃ አይመስልም። መሰረቱን እየናዱ አዲስ ሀገር መገንባት ለጊዜው (ጉልበት ስላለ) የሚመስል ነገር ሊሆን ይችላል – ግን ታሪክ የሚያስተምረን የጊዜ ጉዳይ እንጂ ፍፃሜው እንደማያምር ነው!
የወረስነው ስርዓታዊ ውስብስብ ችግር ላይ ሌላ መቋሰልና ጥላቻ እየጨመራችሁ (አሊያም ማንም እየተነሳ አዛዥ ናዛዥ ሆኖ በአንድነት የድል በአል ገሚሱን ለማስደሰት ገሚሱን ሲያስለቅስ በዝምታ እያለፋችሁ) አቀበቱን የበለጠ ባታከብዱብን መልካም ነበር!