March 3, 2023 

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትን 10ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ/ም በመንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከብሯል።

በትላንትናው ዕለትም ፲ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በማስመልከት ዜና መዋዕል ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክና ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የተሰኙ መጽሐፍት ተመርቀዋል።

መጽሐፍቱ የቅዱስነታቸውን የሕይወት ታሪክ፣ ባለፉት ፲ ዓመታት በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገራት ያከናወኗቸውን ዋና ዋና ሥራዎችን፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችን፣ ቤተ ክርስቲያን ባለፉት ፲ ዓመታት በስኬት ያከናወነቻቸው ዋና ዋና ተግባራት እና የገጠሟትን ተግዳሮቶች ተከትሎ በቅዱስ ፓትርያርኩ የተላለፉ መልዕክታትን አጠቃሎ የያዘ መሆኑ ተገልጿል።