March 4, 2023 – Zemedkun Bekele

የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ወደ ኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ቢሮ ለስብሰባ ተተርተው መሄዳቸውን ዘመድኩን በቀለ ተግሮናል። ዘመድኩን በቀለ በሰተን መረጃ መሰረት ሶስቱ ጳጳሳት መንበረ ፕዝፕዝስናቸው በኦሮሚያ ልዩ ሓይሎች የተሰበሩ መሆናቸውን እና በሕገወጥ መንገድ በተሾሙ ጳጳሳት በተባሉ ሰዎች መያዛቸው ይታወቃል። የስብሰባውን ዝርዝር ወደ በኋላ የምንመለስበት ሲሆን ዘመድኩን በቀለ ከታች ያለውን ዝርዝር እንዲያነቡ ጋብዟል።

ተጠርተው ሄደዋል…!  በዘመድኩን በቀለ

“…በኦሮሚያ ቢሮ የሚሠሩ ወፎቼ ይህን ብለውኛል። የኦሮሚያው ፕሬዘዳንት ሽመልስ አብዲሳ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ወደ ቢሮው ጠርቷቸው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱም ወደዚያው ሄደዋል። የእኔ ወፎችም በዚያው ናቸው። ሃገረ ስብከታቸው በኦሮሚያ ከሆኑ ሊቃነ ጳጳሳት መካከል በስም የተጠቀሱ እንደታዩ ሲሆን የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ጨምሮ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ፣ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ፣ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ፣ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል እና ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ናቸው።

“…ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ አቡነ ሩፋኤል፣ አቡነ እንጦንስ መንበረ ጵጵስናቸው የተሰበረ ሲሆን ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን ወፎቼ ሲገቡ ያላዩዋቸው መሆኑን ገልጸዋል።

“…ሽመልስም ሆነ ዐቢይ በፊት በፊት በመንበረ ፓትርያርክ ግቢ በመገኘት ነበር ከአባቶች ጋር የሚወያዩት። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተለይ ሽመልስ አብዲሳ (የደብተራ ድግምት ስለሚያስፈራኝ) ወደ መንበረ ፓትርያርክ አልሄድም። ደግሞም እኔ የመንግሥት ባለ ሥልጣን ነኝ። እነሱ ከማን በልጠው ነው በቢሮዬ የማይስተናገዱት ማለቱ ይነገራል። ሽመልስ የቤተ ክርስቲያኒቱን አጥር ስለነቀነቀ አሁን ባለቤቱን መፍራት አቁሟል። ሽመልስ በዚህ ኦርቶዶክስን በክልሉ በማዋረዱ ተግባር ላይ በሚከተለው የጴንጤ እምነት ተከታዮች ዘንድ እና በኦሮሞ ፅንፈኛ የወሀቢይ እስላሞች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ነው። በተለይ ሁለቱም ጴወሀዎች ሽመልስ ምን ቢበድላቸው እና ቢያስቀይማቸው ኦርቶዶክስን በመግደል፣ በማቁሰል፣ በማፈራረስ፣ በማውደሙ እና በማዋረዱ ተግባር ቁርጠኛ ስለሆነ ሌላ ጥፋቱን ያቻችሉለታል።

• በሰላም ምጡ አባቶቼ…!

• እስቲ አንደዜ ለወፎቼ…👏👏👏👏👏