
5 መጋቢት 2023, 13:06 EAT
ዛሬ እሁድ የካቲት 26/2015 ዓ.ም. በተከናወነው የቶኪዮ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ የበላይነት ይዘው አጠናቀቁ።
በወንዶች የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ሲያጠናቅቁ በሴቶች ደግሞ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
በወንዶች ማራቶን ዴሶ ገልሚሳ 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ 22 ሴኮንድ ውድድሩን በበላይት አጠናቋል።
የ25 ዓመቱ ገልሚሳ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ የማራቶን ውድድር ማሸነፍ የቻለው የአገሩ ልጆች የሆኑትን ሞሐመድ ኢሳ እና ጸጋዬ ጌታቸውን አስከትሎ በመግባት ነው።
ዴሶ ገልሚሳ በወንዶች ማራቶን የዓለማችን 7ኛ ምርጥ አትሌት ደረጃን ለሳምንታት ይዞ የቆየ ሲሆን አሁን ደረጃው 18ኛ ነው።
በውድድሩ ማጠናቀቂያ ኪሎ ሜትሮች ላይ ስድስት አትሌቶች ከሌሎች ተነጥለው በመውጣት ጠንካራ ፉክክር አድርገዋል።
- ስደተኞችን በክህሎት ብቁ ለማድረግ ማሠልጠኛ የከፈተው ኤርትራዊ ስደተኛ5 መጋቢት 2023
- 90+7 የተቆጠረ ጎል፡ የአልሸነፍ ባይነት ምልክት ወይስ ተዘናግተው እንደነበረ ማሳያ?5 መጋቢት 2023
- ዩኬ በትናንሽ ጀልባ ድንበር ለሚያቋርጡ ጥገኝነት አልሰጥም አለች5 መጋቢት 2023
ኬንያዊው ታይተስ ኪፕሩቶ፣ የካናዳው ካሜሩን ሌቪንስ እና ኢትዮጵያውያኔ ዴሶ ገልሚሳ፣ ጸጋዬ ጌታቸው፣ ደመ ታዱ እና ሞሐመድ ኢሳ እስከ ውድድሩ ማጠናቀቂያ ድረስ ትከሻ ለትከሻ ሆነው ሲሮጡ ነበር።
ካናዳዊው አትሌት ሌቪንስ እስከ 39 ኪሎ ሜትር ድረስ እየመራ ቢቆይም 400 ሜትር ብቻ ሲቀር ዴሶ ገልሚሳ ፍጥነቱን በመጨር የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል።
አምስት አትሌቶችን አስከትሎ እስከ መጨረሻዎቹ ኪሎ ሜትሮች ሲመራ የቆየው ካናዳዊ አትሌት በ2 ሰዓት 05 ደቂቃ 38 ሴኮንድ አምስተኛ ሆኖ በመጨረስ የሰሜን አሜሪካ ፈጣኑን ሰዓት ማስመዝገብ ችሏል።
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ደሜ ታዱ ደግሞ 6ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
በሴቶች የማራቶን ውድድር ደግሞ ኬንያዊቷ አትሌት ሮዝመሪ ዋንጂሩ በአንደኝነት ያጠናቀቀች ሲሆን፤ የፕላቲኒየም ደረጃ በሚሰጠው የቶኪዮ ማራቶን ኢትዮጵያውያኑ ሴት አትሌቶች ከ2ኛ እስከ 4ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
ዋንጂሩ 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ 28 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት ውድድሯን ያጠናቀቀች ሲሆን ጸሐይ ገመቹ 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ 56 ሴኮንድ በሁለተኝነት ጨርሳለች።
በባለፈው ዓመት የቶኪዮ ማራቶን ሁለተኛ ሆና ያጠናቀቀችው ኤቴ በከሬ ከሮዝመሪ ዋንጂሩ 2፡34 ሴኮንድ ዘግይታ በመግባት ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
ወርቅነሽ ኢዴሳ ደግሞ 2 ሰዓት 20 ደቂቃ 13 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት አራተኛ ሆና ውድድሯን አጠናቃለች።