የአዲስ አበባ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን አሰልጥኖ መረጃ በማቀበልና በመሰል ስራ ለከተማዋ ሰላም እንዲሰማሩ አድርጊያለሁ ብሎ ነበር ፡፡
ይሁንና ወጣቶች የምንሰጣቸውን መረጃዎች የፀጥታ ሀይሎች ለግል ጥቅም እያዋሉት ነው ይላሉ፡፡ በዚህም በተደራጀ መንገድ ወንጀል እንዲፈፀም ምክንያት ሆኗል ይላሉ፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ በበኩሉ በፀጥታ መዋቅሩ የስነ ምግባር ችግር ያለባቸው ካሉ አፀዳለሁ የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡