በደቡብ ክልል በደራሼ ልዩ ወረዳ ሆልቴ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ከፌደራል ፖሊስ በክህደት ተቋሙን ለቀዋል የተባሉ ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት ተሽከርካሪ በኃይል በማስቆም ፈፅመውታል በተባለ ዘረፋና፤ የዘረፋ ወንጀል ሙከራ ተጠርጥረዉ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ፖሊስ አስታዉቋል።
ከአርባምንጭ ወደ ኮንሶ የሚወስደዉ አዉራጎዳና ድንጋይ ደርድረዉ በመዝጋት ተሽከርካሪ በማስቆም በተደጋጋሚ በተፈፀሙ ዘረፋዎችና የዘረፋ ሙከራ ወንጀል ሁለቱ የፖሊስ አባላት እጃቸዉ እንዳለበት ከህብረተሰቡ ለልዩ ወረዳዉ ፖሊስ በተሰጠ ጥቆማ መነሻ ተጠርጣሪዎች የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም በፖሊስ መያዛቸዉ ነዉ የተነገረዉ።
ፖሊስ በአካባቢያዊ ማስረጃ ተመርኩዞ የያዛቸዉ ሁለቱ የቀድሞ ፖሊስ አባላት ላይ በአፋጣኝ ምርመራ አጣርቶ ለህግ በማቅረብ የቅጣት ዉሳኔ ሊያሰጥ የሚችል ፖሊሳዊ ስራ አየሰራ መሆኑን ከደቡብ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ደቡብ ፖሊስ