
ከ 8 ሰአት በፊት
በ22 ሳምንት (አምስት ወር ከሳምንት) እርግዝና የተወለዱት ካናዳዊ ወንድምና እህት በጊነስ የድንቃ ድንቅ መዝገብ ሰፈሩ።
ጨቅላዎቹ የዓለማችን ያለጊዜያቸው የተወለዱ መንትዮች የሚል ስያሜም አግኝተዋል።
አዲያህ እና አድሪያል በተጸነሱ በ126ኛ ቀናቸው ነው የተወለዱት።
ጨቅላዎቹ ከ22 ሳምንታቸው በአንድ ሰዓት ባነሰ ጊዜ ቢወለዱ ኖሮ በህይወት የመወለድ ተስፋቸው የመነመነ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ሆስፒታሉም ህይወታቸውን ለመታደግ አይሞክርም ነበር ሲል ጊነስ አስታውቋል።
ሙሉ እርግዝና የሚባለው ዘጠኝ ወራት (40 ሳምንታት) የሚቆይ ሲሆን እነዚህ ጨቅላዎች መወለድ ከነበረባቸው በ18 ሳምንታት ቀድመው ነው የተወለዱት።
እናታቸው ሻኪና ራጄንድራም በ21 ሳምንት ከአምስት ቀናት ላይ ምጥ ሲጀምራት ዶክተሮቹ ህጻናቱ በህይወት የመወለድ እድላቸው በከፍተኛ ደረጃ የመነመነ እንደሆነ እንደነገሯት ታስረዳለች።
ለሻኪና ይህ ሁለተኛዋ እርግዝና ሲሆን ከወራት በፊትም ነው ኦንታሪዮ በሚገኝ ሆስፒታል ጽንሷ የጨነገፈው።
አባታቸው ኬቨን ራዳራጃህ በበኩሉ ሆስፒታሉ እንዲህ ያለ እርግዝናን መርዳት ከባድ እንደሆነም ስለነገሯቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳዘነውና፣ እያለቀሰም ይጸልይ እንደነበር ተናግሯል።
- ከአንድ ሚሊዮን በላይ ፈረንሳዊያን በመላ ሃገሪቱ የሥራ አድማ ሊመቱ ነውከ 9 ሰአት በፊት
- እስከ 18 ዓመቱ ማንበብ እና መጻፍ ሳይችል የቆየው በእድሜ ትንሹ ፕሮፌሰር ለመሆን በቃከ 9 ሰአት በፊት
- የዩኬ አገር ውስጥ ሚኒስቴር ሕገወጥ ስደተኞችን እንዲያባርር ልዩ ሥልጣን ተሰጠውከ 8 ሰአት በፊት
በርካታ ሆስፒታሎች ከ24 እስከ 26 ሳምንታት ያሉ እርግዝናዎችን ለማዋለድ አይሞክሩም።
ነገር ግን ጥንዶቹ እድለኛ ሆነው ቶሮንቶ የሚገኘው የሲናና ተራራ ሆስፒታል የአራስ ህጻናት ልዩ እንክብካቤም መዛወር ቻሉ።
ሻኪና በሁለተኛዋ ቀን ምጥ፣ 21 ሳምንታት ከስድስት ቀን እርግዝና ላይ ልጆቹ ከ22 ሳምንታት ጥቂት ደቂቃዎች በፊት ከተወለዱ ሆስፒታሉ ህይወታቸውን ለመታደግ እንደማይሞክርና መሞታቸው እንደማይቀርም ተነግሯታል።
ከፍተኛ የደም መፍሰስ ቢያጋጥም ጨቅላዎቹን ለተወሰኑ ሰዓታት በማሕጸኗ ውስጥ እንዲቆዩ ለማድረግ የተቻላትን ያህል ሁሉ ጥረት አድርጋለች።
ሆኖም የሸርት ውሃዋ ሌሊት ላይ የፈሰሰ ሲሆን 22 ሳምንት ሊሞላቸው ሁለት ሰዓት ሲቀረው ነው የተወለዱት።
በአሁኑ ወቅት አድያ እና አድሪያል አንድ ዓመት ሊሞላቸው ሲሆን በከባድ የጤና ችግርም ታጅበው ነው እዚህ የደረሱት።
“ህጻናቱ በሞት አፋፍ ላይ ሆነው በርካታ ጊዜ አይተናቸዋል” ብላለች እናታቸው። ህጻናቱ በአሁንም ወቅት ዶክተሮች የቅርብ ክትትል እያደረጉላቸው ቢሆንም በጥሩ ሁኔታ ላይ ናቸው ተብለዋል።