March 9, 2023 

ኢዜማ ከየካቲት 22 ጀምሮ “ያላግባብ ታስረውብኛል” ያላቸውን ስድስት አባላቱን መንግሥት ባስቸኳይ እንዲፈታ መጠየቁን ዶይቸቨለ ዘግቧል።

ፓርቲው ታሠሩብኝ ካላቸው አባላቱ መካከል፣ አምስቱ ለደቡብ ክልል ምክር ቤት በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አካባቢን የወከሉ መሆናቸውን ገልጧል ተብሏል።

ታሳሪዎቹ በሕጉ መሠረት ለፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ፓርቲው ገልጧል ተብሏል። የክልሉ ፍትህ ቢሮ፣ በታሳሪዎቹ ላይ የደረሰኝ የወንጀል ምርመራ ወይም የክስ ሪፖርት የለም ማለቱን ዘገባው አመልክቷል።

ከጉራጌ ዞን የክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ፣ ባለፉት ሳምንታት የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በርካታ ሰዎችን እንዳሰሩ ሲዘገብ ቆይቷል።

የድምጽ ዘገባው የዶቼቬሌ ነው።