March 9, 2023 

Hundreds of Ugandan sect members flee to Ethiopia, fearing doomsday . Leaders of sect convinced them that end of world is near and death is about to strike their area

የተመድ የሰብዓዊ መብት የባለሙያዎች መርማሪ ቡድን የቆይታ ጊዜ እንዲቋረጥ ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳላትም በሳምንታዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ተነስቷል

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የአሜሪካ እና ኢትዮጵያን ግንኙነት የበለጠ እንደሚያሳድገው ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ አምባሳደር መለስ አለም በሳምንታዊ መግለጫቸው ያነሱት።

የዓለም ፍጻሜ ዱርሷል በሚል ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል ስለተባሉት ኡጋንዳዊያን፣ ስለ ተመድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራ፣ የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ በዓረብ ሊግ ጉባኤ ላይ ስላሰሙት ንግግር እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ቃል አቀባዩ መግለጫ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ከሰሞኑ ከ100 በላይ ኡጋንዳዊያን የዓለም ፍጻሜ ደርሷል ፣መድህን የሚገኘውም በኢትዮጵያ ነው በሚል ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል ስለተባሉት የሀይማኖት ሰዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

ዜናውን እንደሰሙት የተናገሩት አምባሳደር መለስ “በተባለው ልክ ከኡጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የሚያሳይ ነገር የለም፣ ከወትሮው የተለየ ቁጥር ያላቸው ኡጋንዳዊያን ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የሚያሳይ ነገር የለም” ብለዋል።

Hundreds of people belonging to a religious sect in eastern Uganda have fled from their villages to Ethiopia, Ugandan police said Sunday.

Police said that according to their investigations, the sect members fled to escape the end of the world, which they believe will start from their area.

They said the members of the sect were told by its leaders that their area would soon be hit with death and all the people there would die. They reportedly sold off their property and fled to Ethiopia, from where they are communicating with some of their relatives in Uganda.

https://www.aa.com.tr/en/africa/hundreds-of-ugandan-sect-members-flee-to-ethiopia-fearing-doomsday/2837933

የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሳሜህ ሽኩሪ በአረብ ሊግ ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የተናጠል እርምጃ እየወሰደች እንደሆነ መናገራቸውን አምባሳደር መለስ ተችተዋል።

ቃል አቀባዩ “የግብጽ አቋም ኋላቀር እና ጊዜውን የማይመጥን ነው፤ ስለ ህዳሴው ግድብ አሁን ላይ መናገር የሚያስችል ምንም አዲስ ነገር የለም፤ ግንባታው በራስ ሀብት ህዝብን ለመጥቀም ተብሎ የተጀመረ እና አሁንም የቀጠለ ነው” ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለኢትዮጵያ ያቋቋመው የሰብዓዊ መብት ምርመራ የባለሙያዎች ቡድን ዓላማው ፖለቲካዊ ስለሆነ ቆይታው እንዲቋረጥ ኢትዮጵያ ትፈልጋለችም ሲሉ ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

አል-ዐይን ለአማርናው  አናዶሉ ለእንግሊዘኛው