March 10, 2023 – Getachew Shiferaw
የሰላም ስምምነቱ ተጥሶ የወረራ ዝግጅት እየተደረገ ነው!

በሰላም ስምምነቱ መሰረት እስካሁን የትግራይ አካባቢዎች በመከላከያ መያዝ ነበረባቸው። ጭራሽ ሰራዊቱ ህይዎት ገብሮ ከያዛቸው ቦታዎች እንዲወጣ ተደርጓል።
የትህነግ ታጣቂ መሳርያ መፍታት ነበረበት። አስረከበው የተባለው ከባድ መሳርያ ቀለም የቀባ የማይሰራ መሳርያ ነው። ቀሪው ትህነግ እጅ ነው። የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳርያን ጭራሽ ለይምሰልም አላስረከበም። ትህነግ በዋግምኸራ በኩል በቅርቡ ጥቃት የፈፀመው በቡድን መሳርያ ጭምር ነው። በጠለምት፣ ራያ አዋሳኝ አካባቢዎች የትህነግ ታጣቂ ስልጠና ላይ ነው። በሁሉም አካባቢዎች ለወረራ ተዘጋጅቷል።
ከሱዳን መንግስት ጋር በተደረገ ስምምነት ሱዳን ውስጥ እየንቀሳቀሱ ኢትዮጵያን ሲያጠቁ የነበሩ ታጣቂዎችን አልደግፍም ብላ ስታስወጣ፣ ትህነግ ግን አሁንም ስልጠና ላይ ነው። በቅርቡ ካርቱም በተከበረ የካቲት 11 በዓል በሱዳን ለሚገኘው የትህነግ ታጣቂ ገንዘብ ተዋጥቶ፣ ተጨማሪ ኃይል እንዲመለምልና እንዲያሰለጥን ተደርጓል። ሱዳን ሆነው የትህነግ ታጣቂን የሚያደራጁ አዲስ አበባ ደርሰው ወደ ሱዳን ተመልሰዋል። ትግራይ የነበሩ የታጣቂው አመራሮች ከትግራይ አዲስ አበባ መጥተው ወደ ሱዳን እንዲሄዱ ተደርገዋል።
የትህነግ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኞች በአማራና አፋር ላይ አዲስ ዘመቻ ከፍተዋል። ከስምምነቱ ውጭ ትህነግ ለወረራ እንዲዘጋጅ እድል ተሰጥቶት እየተዘጋጀ ነው።
ያላወቁት ግን የአማራና የአፋር ህዝብ ራሱን መከላከል ብቻ ሳይሆን ሰራዊትና አገርን ያዳነ ህዝብ ነው። በእንዝላልነት ያስመቱትን ሰራዊት ከትህነግ ጥቃት አትርፎ ወረራ የቀለበሰው የአማራ ህዝብ ነው።
–