
በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ድጋፍ ለማድረግ በቡድንም ሆነ በተናጠል መሰብሰብ እንደማይፈቀድ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ማሳሰቢያ አወጣ። የሚሰበሰበዉን ድጋፍ በአግባቡ ለማስተዳደር፣ ፍትሓዊ በሆነና ግልፅነት ባለዉ መንገድ ለችግር ለተጋለጡ ወገኖቻችን ተደራሽ ለማድረግ ከዚህ ቦኋላ ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እዉቅና ዉጭ በቡድንም ሆነ በተናጠል ድጋፍ ማድረግ አይፈቀድም ብሏል።
በክልሉ በአንዳንድ ዞኖች በተለይም በቦረና ዞን በተከታታይ አምስት የዝናብ ወቅት ዝናብ አለመጣሉን ተከትሎ በተከሰተዉ ድርቅ ምክንያት መንግስት ባቀረበዉ ጥሪ መሠረት ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች በተለያዩ መንገዶች በገንዘብና በአይነት ድጋፍ እየተሰበሰበ እንደሚገኝ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ የሚሰበሰበዉን ድጋፍ በአግባቡ ለማስተዳደር፣ ፍትሓዊ በሆነና ግልፅነት ባለዉ መንገድ ለችግር ለተጋለጡ ወገኖቻችን ተደራሽ ለማድረግ ከዚ ቦኋላ ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወይም ከኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ እዉቅና ዉጭ በቡድንም ሆነ በተናጠል ድጋፍ ማድረግ የማይፈቀድ መሆኑን እናሳዉቃለን።