March 13, 2023 – Konjit Sitotaw

(መረጃ.ኮም ) – የአብይ አስተዳደር አዲስ አበባን ጨፍልቆ ከጥቅም ውጪ ለማድረግ እና ነዋሪዎቿን በድሕነት ለመቅበር እየነደፈ ያለው እቅድ እንደቀጠለ ነው ፤ የሚናገረውና የሚሰራው የማይገናኘው ኦህዴድ መራሹ የአብይ አስተዳደር አዲስ አበባን ለማድቀቅ ካቀዳቸው እቅዶች አንዱ የሸገር ከተማን በዙሪያው ማቋቋም ሲሆን በዚህ መሰረት ተቋቁሞ ከንቲባ ተሹሞለት ስራ ጀምሯል፤ የመጀመሪያ ስራው የኦሮሞ ተወላጅ ያልሆኑ ዜጎች መኖሪያ ቤቶች ማፍረስና የኦሮሞ ተወላጅ ላልሆኑ ዜጎች ኦሮሞዎች ቤት እንዳያከራዩ ማደርግ ሲሆን በዚሁም መሰረት በርካታ ቤቶችን በማፍረስ እና የፈረሰባቸው ዜጎች ከኖሩበት ቀየ ሲፈናቀሉ ቤት የሚያከራያቸው እንዳያገኙ አድርጓል አሁንም ቀጥሎበታል
በመቀጠልም በሸገር ከተማ የታቀፉ የተባሉ ነጋዴዎችን እና የተሽከርካሪ ባለንብረቶችን ከአዳነች አቤቤ ትራንስፖርት ቢሮ ጋር ሆኖ ማገድ እና ማሳደድ ነበር ከባለ ሶስት እግር ባጃጅ ጀምሮ እስካሁንም ቀጥሎበታል። እንዲሁም በአዲሱ የሸገር ከተማ አከባቢ ያሉ የመንግስት ሰራተኛ ያልሆኑ ዜጎችን ከስራቸው አፈናቅሎ በምትካቸው ኦሮሚኛ ተናጋሪ ካድሬዎችን መቅጠር ስለሆነ ይህንንም እያደረጉት ነው። በቀጣይነት በርካታ ዜጎችን ለማንገላታት እና ለማሰቃየት የታቀዱ ሕጎች እንዳሉ ለከተማዋ ከንቲባ ቅርብ የሆኑ አንድ የቢሮ ኃላፊ ለመረጃ ኮም ጋዜጠኛ ነግረውታል።
በዚህም መሰረት በቀጣይነት ከአራቱም ማዕዘን የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ወደ አዲስ አበባ መግባት ከፈለጉ ለጫኑት እቃ ቀረጥ እንዲሁም መንገደኞች የኮቴ ለሸገር ከተማ አስተዳደር እንዲከፍሉ ሊደረግ መሆኑን እኚሁ የቢሮ ኃላፊ ይናገራሉ። በሸገር ከተማ ከንቲባ ዶክተር ተሾመ አዱኛ ጠረጴዛ ላይ ቀርቦ ያለው እና በአዳነች አቤቤ በመራቸው ምስጢራዊ ስብሰባ ላይ መመሪያ የተሰጠ ሲሆን ቀረጡና የኮቴ ክፍያ በትንሽ ገንዘብ እያለማመዱ ማስፋፋት እንዲሁም እቃዎችን ኮንትሮባንድና ህገወጥ በሚል መውረስ እንደሚሆን መመሪያ ተሰቷል።
ይህ መመሪያ ጸድቆ በይፋ በቅርቡ እንደሚሰራበትና የከተማው የጸጥታ ኃይል ተጠናክሮ ሲያልቅ እንደሚጀምር ተነግሯል። ከከተማዋ አስተዳደር የተከለከለ ሰው ሸገር ከተማን እንደማያልፍና ማንኛውም ወደ አዲስ አበባ መግባት የሚፈልግ ሰው ወደፊት በሚወጣ መመሪያ መሰረት እንዲስተናገድ ይደረጋል ተብሏል። ወደፊት ይወጣል የተባለው መመሪያ ምን ይመስሎታል ተብለው የተተየቁት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱት የቢሮ ሃላፊ እንዳሉት ምናልባት የአዲስ አበባ መታወቂያ ያሌላቸው ከክልላቸው ደብዳቤ አፅፈው ካልመጡ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ይከለከላሉ ነጋዴዎችም ከሆኑ ይዘው የመጡት ንብረስ እንዲወረስ ይታዘዝ ይሆናል ያሉ ሲሆን ይህ መመሪያ ተጣናክሮ ከቀተለ በቀጣይነት የክፍለሃገር ነጋዴዎች ከአዲስ አበባ ገዝተው ለሚሄዱት ፍጆታዎች ሸገር ከተማን አቋርጠው ስለሚሄዱ ለሸገር ከተማ የተወሰነ ግብር ይከፍላሉ ብለዋል። የቢሮ ኃላፊው አክለውም ወደፊት ሸገር የሚለው ቃል እንደሚቀየር ተናግረዋል፤ አሁን ሸገር የተባለበትም ምክንያት ሕዝቡን ለማለዘብ እንደሆነ ይናገራሉ። ዘገባው የመረጃ ኮም ነው።