
ከ 2 ሰአት በፊት
በስህተት ወደ ባንክ ሂሳቧ የገባውን ከፍተኛ ገንዘብ ለግል ጥቅሟ በማዋል በሌብነት ዘብጥያ ወርዳ የነበረችው ደቡብ አፍሪካዊት የአንድ ዩኒቨርሲቲ የግምጃ ቤት [ገንዘብ ቤት] ኮሚቴ ሆና ተሾመች።
ሲቦንጊሌ ማኒ ከአምስት ዓመታት በፊት ተማሪ ሳለች 1400 ራንድ የኪስ ገንዘብ ሊከፈላት ሲገባ በስህተት 1 ሚሊዮን ዶላር በባንክ ሂሳቧ ገቢ ተደርጎላት ነበር።
ማኒ ገንዘቡን ገቢ ላደረገው የተማሪዎች የፋይናንስ ድጋፍ ሰጪ ተቋም ስህተቱን በማሳወቅ ተመላሽ ከማድረግ ይልቅ ገንዘቡን ወጪ በማድረግ ለተለያዩ የግል ወጪዎቿ አውላ ነበር።
ገንዘቡ ወደ ሂሳቧ እንደገባ ሞባይል ስልኮች፣ ውድ ጌጣ ጌጦች፣ የአልኮል መጠጥ ስትገዛ ቆይታለች። ስህተቱ ታውቆ የባንክ ሂሳቧ እንዳይንቀሳቀስ እስኪደረግ ድረስ በ73 ቀናት ውስጥ በመላ አገሪቱ በሚገኙ 48 ቦታዎች 70 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወጪ አድርጋ ነበር።
- ሻክሮ ለቆየው የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ግንኙነት የአንቶኒ ብሊንከን ጉብኝት ምን ይዞ ይመጣል?14 መጋቢት 2023
- ሕጻናት ለምን በተደጋጋሚ ለቶንሲል ህመም ይዳረጋሉ?14 መጋቢት 2023
- ሞት ተፈርዶባቸው ለ50 ዓመታት የታሰሩት ጃፓናዊ ጉዳይ እንደገና ሊታይ ነውከ 5 ሰአት በፊት
ሲቦንጊሌ ማኒ በቁጥጥር ሥር ከዋለች በኋላ በሌብነት ወንጀል ጥፋተኛ ተብላ አምስት ዓመታትን በእስር እንድታሳለፍ ተፈርዶባት ነበር።
ይሁን እንጂ ማኒ የእስር ጊዜዋን ሳታጠናቅቅ በአመክሮ ከማረሚያ ቤት መለቀቋን የደቡብ አፍሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ይህ የኋላ ታሪኳ እያለ አሁን ላይ ማኒ የዋልተር ሲሱሉ ዩኒቨርሲቲ የግምጃ ቤት ኮሚቴ ተደርጋ መሾሟ መሾሟ ተሰምቷል።
ማኒ የዩኒቨርሲቲው ግምጃ ቤትን ለመምራት በማኅብራዊ ሚዲያዎች ጭምር ቅስቀሳ ስታደርግ ነበር። በአንድ የምርጫ ፖስተር ላይ “ሲቦንጊሌ ማኒ ለግምጃ ቤት!” በሚል መፈክር ድምጽ እንዲሰጣት ጠይቃለች።
ለግምጃ ቤት ኃላፊነት ቦታ ከተሰጠው 108 ድምጽ ማኒ 79 ድጋፍ ማግኘቷን የደቡብ አፍሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የማኒ ሹመት በሳምንቱ መጨረሻ ከሚካሄደው ድጋፍ የመስጠት ሂደት በኋላ የሚጸና ይሆናል።