
ከ 3 ሰአት በፊት
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2030 የሚካሄድን የዓለም ዋንጫ ለማዘጋጀት ሞሮኮ ትላንት በይፋ ጥያቄዋን አቀረበች።
ጥያቄዋን ለፊፋ በይፋ ያረበችው ሞሮኮ የዓለም ትልቁን የእግር ኳስ ሁነት የምታዘጋጅ ሁለተኛዋ የአፍሪካ ሀገር ለመሆን ተስፋ አድርጋለች።
ሞሮኮ ውድድሩን ለማዘጋጀት ጥያቄ ስታቅብ ይህ ለስድስተኛ ጊዜ ነው።
ሞሮኮ ወድድሩን ለማዘጋት ያላት ፍላጎት ሩዋንዳ በተካሄደ ሥነ-ስርዓት ይፋ የተደረገ ሲሆን ከ8 ዓመታት በኃላ የሚካሄድውን ውድድር በጣምራ ለማዘጋጀት ጥያቄ ካቀረቡበት ስፔንና ፖርቹጋል ጋር ትፎካከራለች።
ባለፈው ወርም አርጀንቲና፣ ቺሊ፣ ፓራጓይና ኡራጓይ ወድድሩን በጣምራ እንዘጋጅ የሚል ጥያቄ አቅርበዋል። ሀገራቱ ውድድሩ የተጀመረበትን 100ኛ ዓመት በተጀመረበት ኡራጋይ ይካሄዳል የሚል ተስፋ ሰንቀዋል።
- ባለ ብሩህ አእምሮ ወጣቶችን እያፈሩ ያሉት የኢትዮጵያ የአዳሪ ትምህርት ቤቶችከ 5 ሰአት በፊት
- በሃላባ ከትምህርት ቤት ተወስዳ የታሰረችው ታዳጊ እና የቀረበባት ክስከ 5 ሰአት በፊት
- የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን አዲስ አበባ ገቡከ 4 ሰአት በፊት
የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በኳታር በተካሄደው የዓልም ዋንጫ በነበረው የጨዋታ እንቅስቃሴ ከመላው አፍሪካ ደጋፊዎችን አግኝቶ የነበረ ሲሆን ውድድሩንም በአራተኝነት ጨርሷል።
በተጨማሪም በአፍሪካ እግር ኳስ ምርጡን ደረጃም ያገኘ ቡድን ሆኗል።
ዓለም ዋንጫን የማዘጋጀት መደበኛው ጥያቄ በቀጣዩ ሰኔ የሚጀመር ሲሆን አዘጋጁ የሚታወቀው ከ3 ወራት በኃላ ይሆናል።
አፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ ያዘጋጀችው ከ13 ዓመታት በፊት በደቡብ አፍሪካ ነበር።
የ2026 የዓለም ዋንጫን ካናዳ፣ አሜሪካ እና ሜክሲኮ በጋራ ያዘጋጁታል።