
ከ 47 ደቂቃዎች በፊት
በኡጋንዳ ዋና ከተማ አቅራቢያ ወዳለ አንድ ትምህርት ቤት ክፍል ጥሶ የገባ ከባድ መኪና ሦስት ተማሪዎችን ገደለ።
ከባድ የጭነት ተሽከርካሪው ከዋና ከተማዋ ካምፓላ 130 ኪሎ ሜትሮች ርቃ በምትገኘው ጎምቤ በተባለችው አካባቢ ነው አደጋውን የደረሰው።
በአደጋው ከሞቱት ሦስት ተማሪዎች በተጨማሪ በክፍሉ ውስጥ የነበሩ ቢያንስ 18 ተማሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
አደጋውን ተከትሎ የኡጋንዳ ፖሊስ እንዳለው የጭነት ተሽከርካሪው ከአሽከርካሪው ቁጥጥር ውጪ ከሆነ በኋላ የትምህርት ቤቱን አጥር ጥሶ ገብቷል።
በትምህርት ቤቱ ውስጥም በርካታ ተማሪዎች የነበሩበትን የኮምፒውተር ቤተ ሙከራን ግማሽ ጎን አፍርሶ በመግባት በሕይወት እና በአካል ላይ ጉዳት አድርሷል።
የከባድ መኪናው ግማሽ አካል ተማሪዎች የነበሩበትን ክፍል ጥሶ በመግባት የክፍሉን ጣራም ገነጣጥሎታል።
- ባለ ብሩህ አእምሮ ወጣቶችን እያፈሩ ያሉት የኢትዮጵያ የአዳሪ ትምህርት ቤቶችከ 5 ሰአት በፊት
- የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን አዲስ አበባ ገቡከ 5 ሰአት በፊት
- በሃላባ ከትምህርት ቤት ተወስዳ የታሰረችው ታዳጊ እና የቀረበባት ክስከ 5 ሰአት በፊት
አደጋ ያደረሰውን የጭነት መኪናን ሲያሽከረክር የነበረው የ26 ዓመት ሾፌር በቁጥጥር ስር ውሎ በፖሊስ ምርመራ እየተደረገበት ነው።
አደጋውን ተከትሎ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ ውስጥ የሚካሄደው የመማር ማደስተማር ሂደት እንዲቋረጥ ተደርጎ ተማሪዎች ለአንድ ሳምንት በቤታቸው እንዲቆዩ ታዘዋል።
በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ስላሉ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
አደጋውን ያደረሰው ሲኖትራክ በመባል የሚታወቀው ከባድ የጭነት መኪና መሆኑን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ተናግረዋል።
ከተማሪዎች በተጨማሪ በኮምፒውተር ቤተ ሙከራው ውስጥ የነበሩ አንዲት መምህርም የእጅና የእግር መሰበር ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ከአንድ ሳምንት በፊት እዚያው ኡጋንዳ ውስጥ አንድ ከባድ መኪና ከአንድ ትምህርት ቤት አጥር ጋር ተጋጭቶ የሰባት ዓመት ታዳጊ ተማሪን ለሞት ዳርጓል።