
ከ 4 ሰአት በፊት
የአሜሪካ መንግሥት ቲክቶከ የግድ መሸጥ አለበት ያለ ሲሆን ያ የማይሆን ከሆነ ግን በሀገሪቱ ሊታገድ እንደሚችል ሪፖርቶች ጠቁመዋል።
ባለቤትነቱ ባይትዳንስ የተባለ የቻይና ኩባንያ የሆነው የአጫጭር ቪዲዮዎች ማጋሪያው ቲክ ቶክ በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ተጠቃሚዎቹ መረጃን በመሰብሰብ በአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ላይ አደጋ ጋርጧል የሚል ክስ ይቀርብበታል።
ኩባንያው ባለቤትነቱን እንዲያስተላልፍ ጥያቄ እንደቀረበለት ዋል ስትሪት ጆርናል ቀደም ብሎ የዘገበ ሲሆን ቲክቶክም የዘገባውን እውነትነት ለቢቢሲ አረጋግጧል።
ኩባንያው በጫና እንዲሸጥ ማድረግ በመረጃ ፍሰቱ ላይ ለውጥ አያመጣም ብሏል።
ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ኋይት ሃውስ አስተያየት እንዲሰጥ ቢጠይቅ ምላሽ አላገኘም።
የአሜሪካ መንግሥት ባለስልጣናት በቲክቶክ መተግበሪያ አማካኝነት የሚገኙ መረጃዎች የቻይና መንግሥት እጅ ላይ ሊወድቅ ይችላል የሚለውን ስጋታቸውን ለዓመታት ሲያነሱ ቆይተዋል።
ዋል ስትሪት ጆርናል እንደዘገበው ከሆነ የባይደን አስተዳደር ባይትዳንስ ከቲክቶክ በመራቅ ከቻይና ጋር ያለው ግኝኙነት ግልጽ በሆነ መንገድ እንዲገታ ይፈልጋል።
ጋዜጣው የብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮችን የሚመለከተው የአሜሪካ የውጪ ኢንቨስትመንት ኮሚቴ ባይትዳንስና ቲክቶክ ፍቺ እንዲፈጽሙ ምክረሃሳብ አቅርቧል።
የቲክቶክ ቃለአቀባይ የጋዜጣውን ዘገባ የተቀበለ ሲሆን ኩባንያውን የአሜሪካ የውጪ ኢንቨስትመንት ኮሚቴ እንዳነጋገረው አረጋግጧል።
ነገርግን ቃል አቀባዩ ዘገባው የተጋነነ መሆኑን ጠቅሰው “ፍቺ መፈጸም” በተግባር ሲገለጽ ምን እንደሆነ ግልጽ አያደርግም ብሏል።
- በትግራይ እና በኦሮሚያ ካጋጠመው የጥሬ ገንዘብ እጥረት ጀርባ ያሉ ምክንያቶችከ 5 ሰአት በፊት
- ብሊንከን በጦርነቱ ለተፈጸሙ ጥሰቶች ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጠየቁ15 መጋቢት 2023
- ባለ ብሩህ አእምሮ ወጣቶችን እያፈሩ ያሉት የኢትዮጵያ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች15 መጋቢት 2023
ጨምሮም ዓላማው የብሄራዊ ደህንንትን መጠበቅ ከሆነ ቲክቶክና ባይትዳንስ የሚፈጽሙት ፍቺ ችግሩን አይፈታውም ካለ በኋላ የባለቤት ለውጥ ማድረግ የመረጃ ፍሰቱ ላይ የሚጨምረው አዲስ ቁጥጥር አይኖርም ሲል ገልጻል።
“የብሄራዊ ደህንንትን ስጋት ለመቅረፍ አስተማማኙ መንገድ መሰረቱን አሜሪካ ያደረገ የአሜሪካ ተጠቃሚዎችን መረጃ የሚጠብቅ ስርዓት መዘርጋትና ግልጽ ማድረግ ነው” ሲልም አክሏል።
ቲክቶክ ለመጀመሪያ ጊዜ ይታገዳል የሚል ማስፈራሪያ የደረሰበት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 በዶናልድ ትራምፕ ጊዜ ነበር።
ሆኖም የፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የላላ አቋም አሳይተዋል።
ቲክቶክ እንደ ኢንስታግራምና ትዊተር ሁሉ ከተጠቃሚዎቹ ከፍተኛ መጠን ያለው መረጃዎችን ይሰበስባል።
የተጠቃሚዎችን እንደአሻራ ያሉ መረጃዎችን ከማግኘቱም በተጨማሪ ቦታዎችንም ማወቅ ይችላል። ስጋቱም የሚመነጨው ከዚህ ነው። እነዚህ መረጃዎች በቻይና መንግሥት በኩል ሊያልፉ ይችላሉ ነው።
ቲክቶክ ፕሮጀክት ቴክሳስ በሚል ስያሜ አሜሪካን የሚመለከቱ መረጃዎች በሙሉ ወደ አሜሪካ እንዲዘዋወሩ ስራዎችን መጀመሩን ገልጿል።
ከባንያው በዚህ እቅዱ እንደጸና ለቢቢሲ ገልጿል።