March 19, 2023 – Getachew Shiferaw
2000 አባውራዎች በማንነታቸው ምክንያት ከአዲስ አበባ ሊፈናቀሉ ነው!
አዲስ አበባ “የአርሶ አደር ልጅ” እየተባለ ከኦሮሚያ በርካታ ህዝብ ቤትና መሬት ተሰጥቶታል።
ኮንዶሚኒየም ታድሏል።
–
አገር አፍራሽ ለነበረው ሁሉ መታሰቢያ ወተዘ እየተባለ መስርያ ቤት ተሰጥቶታል። ዋቆ ጉቱ የሚባለው ከዚያድባሬ ጋር ሆኖ አገር ሲወጋ ጀኔራል ጃገማ ኬሎ አንቆ ያመጣው ሰው ስቴዲዬም አካባቢ “ዋቆ ጉቱ ፋውንዴሽን” ተብሎ አንድ ግቢ ተሰጥቶታል። ቦታ ለመያዝ ነው።
–
የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ሰራተኞች ቤት ተሰጥቷቸዋል።
በርካታ ሺህ መምራን ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ተደርጓል።
የሀሰት መታወቂያ የተሰራለት ሁሉ ቦታና ቤት ተሰጥቷቸዋል።
የፈለጉትን ሁሉ አድርገው የቀረውን የህፃናት ኳስ መጫዎቻ ሜዳ ሳይቀር አርሶ አደሩ ገብቶ እንዲያርሰው አድርገዋል።
ከተማ ውስጥ የፈለጉትን ሲሰገስጉ ህገወጥነት አልተባሉም። አርሶ አደሩን እግር ኳስ ሜዳ እረስ ሲሉት ህገወጥ አልተባለው። ኮንዶሚኒዬም በአጣና ሲቀሙ ህገወጥ አልተባለም። ህዝብ በቁጠባ የሰራውን ቤት ለራሳቸው ሰው ሲያድሉ ህገወጥ አልተባለም። አማራዎች በገንዘባቸው የሰሩት ህጋዊ ቤት ግን ህገወጥ ተብሎ እየፈረሰ ነው። ህገወጥ ያስባላቸው ማንነታቸው ብቻ ነው። በአፍሪካ መዲና የዘር ማፅዳት በዚህ መጠን እየተፈፀመ ነው።
–

ሁለቱ ፎቶዎች የሰማይና የምድር ያህል ርቀት አላቸው። የመጀመርያው አዲስ አበባ ላይ ከሚፈርሱት የ2000 አማራዎች ቤት መካከል ነው። ሁለተኛው ፎቶ መሃል አዲስ አበባ አርሶ አደሩ የእግር ኳስ ሜዳንም ሳይቀር አርሰህ ዝራው ተብሎ ሜዳውን ሲያርሰው ነው። አሁን ያለውን ሁኔታ በደንብ የሚገልፅ ነው። አማራው የኖረበት ህጋዊ ቤት በሌሊት እየፈረሰ ይፈናቀላል። ኦህዴድ አርሶ አደሩ ከተማ ውስጥ ያለን የህዝብ ሜዳ በቀን እንዲያርስ ያሰማራዋል።
