March 21, 2023 – Konjit Sitotaw
- ስልጣን ከእጃቸው የወጣ ሰዎች በተለይ አድዋዎች ያስተባበሩት ሰልፍ ነው ተብሎለታል።
በመቀሌና በኩሓ አከባቢ የሚገኙ ሕወሓት ባለፉት ሁለት አመታት በጦርነቱ ያሰማራቸው የትግራይ መከላከያ ሰራዊት አባላት ተብለው የተገለፁ የሕወሓት ወታደሮች መቀሌና ኩሓ አከባቢ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸው ተሰማ ።
እነዚህ በጦርነቱ የተሳተፉ ከመቀሌ እንደስላልሴ እስከ ኩሓ በሚወስደው መንገድ ላይ ሰልፉ የተደረገ ሲሆን የጸጥ ሃይሎች ሰልፉን ለመበተን ሞክረዋል። በሰልፉ ምክንያት በመቀሌ እንደስላሴ አከባቢ ከፍተኛ የትራፊክ መቸናነቅ የታየ ሲሆን የጸጥታ ሃይሎች ሰልፉን በትነው ጭንቅንቁን ለማጥፋት ያደረጉት ሙከራ መክሸፉን የመቀሌ ምንጮች ለመረጃ ኮም ያደረሱት ዘገባ ያስረዳል።
መቀሌ ኩሃ የተጀመረው ተቋውሞ ከጌታቸው ረዳ ፕሬዝዳንትነት መመረጥ ሁለት ቀን በኋላ መከሰቱ እያነጋገረ ነው። የአድዋ ሰዎች ከስልጣን ላይ መነሳት ብስጭት ውስጥ እንደከተታቸው ሲነገር ነበረ። ካምፑን ሲጠብቁ የነበሩ ጠባቂዎች የአድዋው ክንፍ በመሆናቸው ተቃውሞውን እንደሚፈልጉት እየተገለፀ ነው። ህወሓት ያፈነው ሁሉ በዚህ የፖለቲካ ሽኩቻ ወደ ውጪ እየወጣ ነው።
በመቐለ ኩሓ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ መቐለ ዩንቨርስቲ “መለስ ካምፓስ” ታጉሮም ያሉት መንቀሳቀስ የሚችሉና የማይችሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኣካል ጉዳተኞች ከባለፈው እሁድ ጀምረው የሚደረግላቸው እንክብካቤ እጅግ የወረደ በመሆኑ ተቋውሞቻው በማሰማታቸው ኣቶ ጌታቸው ረዳ በኣካል በመሄድ ለማረጋጋት ሞክረው ነበር ሆኖም ዛሬ ገብረ ገብረፃድቃን የሚባለው ሰውዬ ወደ ኣካባቢው ከመጣ በሃላ ምክንያቱ በግልፅ ባልታወቀ ግርግር ተነስቶ የኣጃቢው መሳሪያ በመቀማት ኣጃቢውን ደብድበው ገብረ ገብረፃድቃን ለመግደል የተደረገ ሙከራ ገብረ ገብረፃድቃን ወደ ኣቅራብያው የነበረው ሆቴል በመግባት በጓሮ ዘሎ ብያመልጥም በዚህ ተግባር የተበሳጩ የኩሓ ከተማ ወጣቶችና ኣካል ጉዳተኞች ከኩሓ በኣንድነት ገንፍለው በመውጣት ወደ መቐለ ዋናው ማሃል ከተማ እየተመሙ ይገኛሉ።ኣርሚ 22 የሚባለውም በኩሓ የሚገኘውም የተቋውመው ሰልፉ እንደሚደግፍና ከለላ እየሰጣቸው እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ይገኛል።ዘገባው የመረጃ ኮም ነው ።
ከታች በምስል ይመልከቱት



