March 21, 2023 

በሕገ ወጡ ሹመት ላይ የተሳተፉት ቀሪ 23 ግለሰቦች የይቅርታ ደብዳቤያቸውን ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ለብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እያቀረቡ ይገኛሉ።

በሕገ ወጥ ሹመቱ የተሳተፉ ግለሰቦች ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በመምጣት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ተነጋገሩ።

(EOTC TV //መጋቢት ፲፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ )

በቤተ ክርስቲያን በተፈጸመውን ሕገ-ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ የተሾሙት ግለሰቦች በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ቀርበው ከብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ከብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና በሰሜን አሜሪካ የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጋር በዝግ ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱም ከቅዱስ ሲኖዶስ የተወከሉ ብፁዓን አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ሹመቱን የሰጡት ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በተደረገው ሰፊ ውይይት ስምምነት ባደረጉባቸው 10 ነጥቦች መሠረት በማድረግ መከናወኑን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።