
ከ 1 ሰአት በፊት
የሌሶቱ ፓርላማ በደቡብ አፍሪካ ስር ገብተውብኛል ያላቸውን ሰፋፊ ግዛቶች እንዲመለሱለት በሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ሊወያይ ነው።
በግዙፏ ደቡብ አፍሪካ ተከባ የምትገኘው የትንሽዬዋ አገር ፓርላማ ዛሬ መጋቢት 20/2015 ዓ.ም. በግዛት ጥያቄው ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፍል ተብሎ የሚጠበቀው ዛሬ ነው።
ለፓርላማው የቀረበን የውሳኔ ሃሳብ ሰነድ የጠቀሱ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ የምክር ቤት አባል እንዳሉት፣ ሌሶቱ በዙሪያዋ ያሉ በደቡብ አፍሪካ ስር የሚገኙ በርካታ ግዛቶች ላይ የይገባኛል ጥያቄን አንስታለች።
ሕግ አውጪዎቹ የደቡብ አፍሪካ “ፍሪ ስቴት ግዛትን በሙሉ፣ የሰሜን እና ኢስተርን ኬፕ ግዛቶችን በከፊል፣ ፑማላንጋን በከፊል እንዲሁም የክዋዙሉናታል ግዛትን የተወሰነ ክፍሎችን” የሌሶቶ ግዛት አድርገው እንዲወስኑ ሃሳብ ቀርቧል።
- የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም – አይኤምኤፍ ባለሥልጣናት በኢትዮጵያከ 4 ሰአት በፊት
- በሳዑዲ አረቢያ በሃይማኖት ተጓዦች ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 20 ሰዎች ሞቱከ 4 ሰአት በፊት
- ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሩሲያ እና የቤላሩስ አትሌቶች በፓሪስ ኦሊምፒክ በግል እንዲሳተፉ ሃሳብ አቀረበከ 4 ሰአት በፊት
ሌሶቱ ይገባኛል በሚል ከደቡብ አፍሪካ ለመጠየቅ የተነሳችው አካባቢዎች ደቡብ አፍሪካ ካሏት ዘጠኝ ግዛቶች በአምስቱ ላይ ነው።
የውሳኔ ሃሳቡ ሰነድ እንደሚለው ይህ የሌሶቱ የግዛት ይገባኛል ጥያቄው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በአውሮፓውያኑ 1962 ያሳለፈው ውሳኔን መሠረት ያደረገ ነው።
በንጉሣዊ አስተዳደር ስር ያለችው ሌሶቱ በደቡብ አፍሪካ ሙሉ ለሙሉ ተከባ የምትገኝ ትንሽዬ አገር ስትሆን፣ አጠቃላይ እንቅስቃሴዋ ከደቡብ አፍሪካ ጋር የተያያዘ ነው።
የሌሶቶ ሕዝብ በተጠቀሱት እና አሁን በደቡብ አፍሪካ ስር በሚገኙት ግዛቶች ውስጥ ይኖሩ እንደነበር በታሪክ ይነገራል።

የአገሪቱ ቀደምት ሕዝብ በስፋት ይዘዋቸው ከነበሩት ግዛቶች በጦርነት የተነሳ በኃይል ተገፍቶ ወደ ጠባቡ አሁን ወደ ሚገኙኝበት የሌሶቱ ግዛት ውስጥ እንዲካለሉ ሆነዋል።
አሁን የተነሳው የግዛት ጥያቄም ይህንን መሠረት አድርጎ የሚቀርብ መሆኑ ተጠቅሷል።
ባሶቶ በመባል የሚታወቁት የሌሶቱ ሕዝቦች በደቡብ አፍሪካዎቹ ዙሉ እና ንዴቤሌ ጎሳዎች በተፈጸመባቸው ወረራ ከተበታተኑ በኋላ በአውሮፓውያኑ በ1822 በንጉሥ ሞሼሾይ ቀዳማዊ አማካይነት ነበር የተሰባሰቡት።
ንጉሡ የተበተነውን ጎሳቸውን በአሁኗ ሌሶቱ በማሰባሰባቸው የባሳቶ ሕዝብ አባት በመባል ይታወቃሉ።
ከዘመናት በፊት ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጠቃለዋል የተባሉትን ግዛቶች እንዲመለስ አሁን ሃሳቡ የቀረበ ቢሆንም አገሪቱ ከደቡብ አፍሪካ ጋር የቀረበ ግንኙነት አላት።
ሌሶቱ በድንበር ሙሉ ለሙሉ በደቡብ አፍሪካ በመከበቧ እና በምጣኔ ሀብትም የጠበቀ ቁርኝት ስላላት አንዳንዶች ደቡብ አፍሪካ ውስጥ እንድትካተት ሲጠይቁ ተደምጠዋል።