April 30, 2023 

አብይ አሕመድ ወደ ስልጣን ሲመጣ ሕወሓትን የወነጀለበትና ይቅርታ የጠየቀበትን ወንጀል ራሱ እየፈጸመው ነው።’

የተለመደና ለሕዝብ ጆሮ የሰለቸ ድራማ ከመስራት የተለመደና ለሕዝብ ጆሮ የሰለቸ ክስ ከማቅረብ መንግስት ምናለ ክብሩን ጠብቆ በአዲስ ድራማ ቢመጣ። ……… የፈረደበት ሕገመንግስት፣ ሁሌ ሊናድ ነው ስትሉ በገዛ አፋችሁ የምትሟርቱበት ሕገመንግስት ራሳችሁ የማታከብሩትና የማትታዘዙት ሕገመንግስት ንጽሃንን ለመክሰስና ሃሳባቸውን የገለጹ ዜጎችን ለመወንጀል ትጠቀሙበታላችሁ። መጀመሪያ ራሳችሁ አክብሩት፣ ውደዱት የምትነግዱበትን ሕገ መንግስት ።

በኦሮሚያ ክልል በሰው ሕይወት ቁማር የሚጫወቱ ፖለቲከኞችና ታጣቂዎች በሞሉበት መከሰስ መያዝና መጠየቅ ሲገባቸው መንግስት ነኝ የሚለው አካል ወደ አማራ ክልል በማተኮር አማራን ለማዳከም ሲልም አማራን ሽባ ለማድረግ ሃሳባቸውን በነጻነት በገለጹ ጋዜተኞችና ምሁራን ላይ፣ ሰርተው ነግደው ባተረፉ ባለሃብቶች ላይና በሌሎች ነጻነትና መብትን በተየቁ ሕዝቦች ላይ የሚወሰደ እርምጃ ትክክል አይደለም።

አማራን ሲገለው ከሚውለው ኦነግ ሸኔ ጋር ሲደራደር የሚውለው መንግስት ከሕወሓት ጋር የተደራደረው መንግስት ለምን ከፋኖ ጋር ለመደራደር ፈራ ? ይህ የመንግስት አካሄድ አደገኛና አሸባሪነት ነው። ገሎ አውድሞ ከጨረሰ በኃላ ሊደራደር ከሆነ አሳፋሪ ድርጊት ነው። መንግስት አሁንም ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል። በኢህአዴግ ዘመን ለተፈጸሙ ወንጀሎች ይቅርታ ሲጠይቅ የነበረው አገዛዝ ያንኑ ወንጀሎች እና የሃሰት ክሶች እየደገመው መሆኑ አስደንጋጭ ነው። #MinilikSalsawi

የአማራን ህዝብ ለመምታት ሲባል የተቀነባበረ ድምፅ ጭምር እየተለቀቀ ወንጀልና ፍረጃ ተለምዷል። ግን በዚህ ህዝብን ሊያደናግሩ አይችሉም። ትንሽ ምሳሌ ብቻ ልጥቀስ። Getachew Shiferaw

1) አብዛኛዎቹ የታሰሩት ሚዲያ ላይ በግልፅ በሚሰሩት ስራ ነው። ለምሳሌ እነ ዳዊት በጋሻውንና አሰፋ ኪዳኔን መጀመርያ ስራቸውን እንዲያቆሙ ካሜራና ኮምፒውተሮቻቸውን ነው የዘረፏቸው። መንግስት የሚባለው ወንበዴ አሰማርቶ አዘረፋቸው። “ዘርፈህ ሽጠህ ብላ” የሚል “መንግስት” ነውኮ ያለው። ነገር ግን ተዘርፈውም በቻሉት መጠን ስራቸውን ቀጠሉ። ማስቆም የሚችሉት አስረው መሰላቸው። አሰሯቸው። የእነ ዳዊት በጋሻውን ሙያና ስነ ምግባር የምታውቁ “ሽብር፣ አገር ማፍረስ” ሲባል ሳቅና ንዴት እንደሚቀላቀልባችሁ አልጠራጠርም። ተመልከቱ። እነ ዳዊት በሽብርና አገር ማፍረስ።

2) መሳይ መኮንን በዚሁ ተካትቷል። መሳይ በደንብ እያጋለጣቸው ነው። ያቀናጁት ግን ከ360ዎች ጋር ነው። 360 ያሉ ሰዎች ከእነ መሳይ ጋር ከኢሳት ጀምሮ የተለያዩ ናቸው። እነመሳይን የመንግስት ደጋፊ አድርገው ይወቅሷቸዋል። የጋራ ግብረ ኃይሉ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲወቃቀሱ የሚውሉትን ጭምር አንድ የፖለቲካ አላማ ይዘው ሲንቀሳቀሱ ያዝኳቸው ይላል። በግል ያልታረቁትን፣ የማይግባቡትን።

3) አስቡት ደግሞ ዘመድኩን በቀለ በዕቡዕ ተደራጅቶ ሲሰማ ራሱ የሚጨንቀው ይመስለኛል።

4)

5)…..

እያልኩ መቀጠል እችላለሁ። ኧረ ለዚህ የቂል ድራማ ምን አደከመኝ ብዬ ነው በሶስት የተውኩት።

ይህ ሁሉ ድራማ በአማራ ህዝብ ላይ ለመዝመት ነው። ስልጣን እናቱ የገዛችለት ሽልጦ ይመስል “ሊቀሙኝ ነው” እያለ ሲነፋረቅ የከረመ ኃይል ለዛ ስጋቱ ማርኪያ የሀሰት ፍረጃውን ተያይዞታል። ይህ ሁሉ የመጣው በቤተ ክርስቲያን ላይ እጃቸውን አስገብተው ያልጠበቁት ተቃውሞ ሲያጋጥማቸው ነው። ጉዳዩን ወደ አማራ ዘንበል አድርገው ዘመቻ ጀመሩ። አብዛኛውን ከላይ እንዳልኩት እያጨሱ ነው። በግል ያልታረቁ በርካታ ሰዎች ከዚህ ክስ ውስጥ አሉበት። በእርግጠኝነት አንዳንዶቹ እስር ቤት ሲገናኙም አይነጋገሩም። ይህን የጠቀስኩት ለምሳሌ እንጅ ከስር ያለው አጭሰው አቀነባበርን ያሉት ድራማ ነው።