የአማራ እና የደቡብ ተወላጆች ከስራቸው እየተባረሩ ነው

ከተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የመጡ 86 ፖሊሶች በኮማንደር ደረጃ በሃላፊነት በአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያዎች እና የፖሊስ መምሪያዎች እንዲሁም ወንጀል ምርመራ ካለምንም ማስታወቂያና ቅድመ ዝግጅት ድንገት መመደባቸውን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገለጹ። ሜክሲኮ በሚገኘው የወንጀል ምርመራ ቢሮ ( አዲሱ ማዕከላዊ) የሚገኘው የመረጃ ኮም ምንጭ እንደገለፀለን በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ የፌዴራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤቶች እና ቅርንጫ የፖሊስ መምሪያዎች እንዲሁም በክፍለከተማና በወረዳ ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ ድንገት ከኦሮሚያ ክልል የመጡ ፖሊሶች በቂ የስራ ልምድ እና የፖሊስ ሳይንስ ስልጠና ሳይወስዱ በፖሊስ ሃላፊነት ደረጃ እንዲቀመጡ ተደርጓል ።
በፍጹም ከሰራተኞች ጋር መግባባት ያልቻሉት እነዚህ አዳዲስ በኮማንደር ማዕረግ የተቀመጡ የኦሮሚያ ፖሊሶች የማዕረግ እድገታቸውን ያልጠበቁ እንዲሁም የትምሕርት ዶክመንታቸው በተመደቡበት መስሪያ ቤቶች ያልተያያዘላቸው ሲሆን በዘፈቀደ መተው ቢሮ መረከባቸው በፖሊስ መስሪያ ቤቶች ውስጥ እያነጋገር መሆኑ ተገልጿል ። በተለይ በወንጀል መከላከል በሃላፊነት የተመደቡ ፖሊሶች መስራት አቅቷቸው ሲደናበሩ ተስተውሏል ።
መረጃውን ያደረሰን የፓሊስ አባል ከ15 አመት በላይ ያገለገለ ኮማንደር ሲሆን የዋና ሳጅንነት ማእረግ ሳይኖራቸው ድንገት በኮማንደር ሃላፊነት የተመደቡ የኦሮሚያ ፖሊሶች የስራ መዘበራረቅ መፍጠራቸው አንስቶ ነግሮናል። ይህ የደቡብ ተወላጅ የሆነ ፖሊስ ነገ በስራ ላይ የመቆየት እጣ ፋንታችን አተያያቂ ስለሆነ የራሳችንን መንገድ እንድንፈልግ እየገፉን ነው ብሏል። ኮማንደሩ ይህን መድሎና አመዳደብ አስመልክቶ አብዞኛውን የሌላ ብሄር ከአዲሰ አበባ እያነሱ ባአዳዲስ የኦሮሚያ ተወላጆች በግልጽ እየተኩ ነው ይላል የመጡት ከኦሮሚያ የተመደቡት በአዲስ አበባ ፓሊስ በሁሉም ክፍለ ከተማ መምሪያ ውስጥ ተመድበው ስራ ላይ ናቸው ሲል ተናግሯል። እነዚሁ በብሄራቸው የተመደቡ የኦሮሚያ ፖሊሶች ሙሰኝነትን ከማስፋፋታቸውም በላይ ለእግዝቢት የመጣ እቃ ወደ ቤታቸው በመውሰድና ተገልጋዮችን በማስፈራራት ሕገወጥ ተግባራትን እንደሚፈፅሙ እየተነገረ ነው።
