01/05/2023

የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ሊያጠፋው ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ጦርነት ያወጀበትንና የዘመተበትን የዐቢይ አሕመድ የኦሮሙማ አረመኔያዊ አገዛዝ ፊት ለፊት የሚጋፈጥበት ጊዜው አኹን ነው። 

የአማራን ሕዝብ እንደ ሕዝብ ለማጥፋት አስቦና አቅዶ  የተነሳው የዐቢይ አሕመድ አረመኔያዊ የኦሮሙማ አገዛዝ ቱትሲዎችን እንደ ሕዝብ ለማጥፋት የዘር ማጥፋት ካወጀባቸው የሩዋንዳው የሁቱ  መንግሥት  የከፋ አረመኔያዊ አገዛዝ ነው። የአማራ ሕዝብ ከሩዋንዳው የሁቱ ጨፍጫፊ መንግሥት በሚከፋው የዐቢይ አሕመድ የኦሮሙማ አፓርታይዳዊ አገዛዝ ከታወጀበት ሁሉን አቀፍ የዘር ፍጅት ለመትረፍ ያለው ብቸኛ አማራጭ እንደ ቱትሲዎቹ የአርበኞች ድርጅት አቋቁሞ የታወጀበትን የዘር ፍጅት መጋፈጥ ብቻ ነው።   

የተቀረው አለም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ በየዕለቱ እስከ አስር ሺሕ የሚደርሱ ቱትሲዎችና ለዘብተኛ ሁቱዎች ለሶስት ወራት የተጨፈጨፉበት የሁቱ አገዛዝ የዘር ማጥፋት መቋጫ ያገኘው በወቅቱ የ36 አመት ጎልማሳ በነበሩት ስደተኛ ፖል ካጋሜ የሚመራው የርዋንዳ አርበኞች ግንባር ሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት አሸንፎ አገሪቱን በቁጥጥር ሥር ሲያውል ነበር።

በአገራችንም በዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሙማ አረመኔያዊ አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ እያካሄደው ያለውን የቱትሲ ቅጂ የዘር ማጥፋትና የጅምላ ፍጅት እንዲቆም ማድረግ የሚቻለው የዘር ማጥፋት ጦርነት የታወጀባቸው ግፉአን አማሮች    የዘር ፍጅት ያወጀባቸውን የዐቢይ አሕመድ የኦሮሙማ አፓርታይዳዊ አገዛዝ ተጋፍጠው በማስወገድና አገራቸውን ቁጥጥር ስር ሲያውሉ ብቻ ነው።

ስለዚህ እንደ ቱትሲ  የዘር ማጥፋት ጦርነት የታወጀበት የአማራ ሕዝብ  እንደ ሁቱዎቹ ኢንተርሃሞዮች ከኾነበት የዐቢይ አሕመድ የኦሮሙማው አረመኔ አገዛዝ የዘር ማጥፋት ጦርነት ለመትረፍ ያለው ብቸኛ አማራጭ  በያለበት እንደ ቱትሲዎቹ የአርበኞች ድርጅት ማቋቋምና  እንደ ፖል ካጋሜ አይነት ጀግና የአርበኛ መሪ መሆን ብቻ ነው!