Derartu Tulu
· ከትግራዩ ጦርነት ሳንማር ሌላ ዙር በአማራ ክልል የጦር ውጥረት መግባታችን ሰሜኑን በተራ የማንበርከክ እንጂ አማራ ክልል ከወለጋ በላይ ለሃገሪቱ ስጋት ለዜጎችም የጭፍጨፋና የማፈናቀል ምክንያት ሆኖ አይደለም።
ሕግ ማስከበር በምዕራብም እንጂ በሰሜን አልነበረም። ባለፉት አምስት አመታት እንደ አማራና ትግራይ መከራውን ያየ ሕዝብ የለም። ተፈናቀለ ተገደለ ቤቱ ሕገወጥ በሚል ጭካኔ በላዩ ላይ ፈረሰበት። ቢያኮርፉ የተገላይነት ስሜት ቢሰማቸው አይፈረድም። መንግሥት በጉልበት ከማንበርከክ በፊት ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል።
ዛሬ ሰላምን ቆመን ሳይሆን ተንበርክከን ብንለምንም ሰሚ አጥተን እንደ ጎረምሳ የይዋጣልን እጅጌ መሰቅሰቅ ነገን በፍራቻ የምጠብቀው ቀን ሆኗል። እኛ ወደኋላ ተመልሰን የመቶ ዓመት የጭቅጭቅ ታሪክ ስንማዘዝ ዛሬ ላይ ትውልዱ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ያለምንም ውዝግብ ከነማስረጃው በፎቶ በምስል ይዞ ይህን አምስት ዓመት ለሺ ዓመታት እንደ ሩዋንዳ ሕዝብ በኃዘን ሲዘክረው ይኖራል።
ያኔ እንደ አኖሌ ጨለንቆ ታሪክ የሚያወዛገብ ትውልድ አይኖርም።በቪዲዮ በፎቶ በማን መንግሥት በማን መሪነት በየት አካባቢ ማን ማኅበረሰብ ይህ እንደሆነበት እንደ ዛሬው መጪው ትውልድ ተለያይቶ ሳይሆን በአንድነት በመተቃቀፍ በአንድ ትርክት ይህን ዘመን ሲረግም ይኖራል።ለበለጠ https://t.me/deratulu2