May 4, 2023 – Konjit Sitotaw 

May be an illustration of 1 person

የጀግናው አረበኛ መሳፍንት ተስፉ መልዕክት!!

ሚያዝያ 25/2015 ዓ.ም

መላው ህዝባችን ዕውነቱን ለይቶ ይረዳ።

እኛ የአንድ ቡድን ግፍና ጭቆናን በደምና አጥንታችን ታግለን የለውጥ ተስፋ ፈንጥቀናል።የጠላትን ወረራ መክተናል።

የህዝባችን የመብት ጥያቄዎች ሳይመለሱ በትዕግስት ቆይተናል።ንፁሃን አልበደልንም፤ጫካም አልሸፈትነም፤ባንክም ሆነ ታንክ አልዘረፍነም፤መንገድ ዘግተን ኬላ ጥለን ቀረጥ አልሰበሰብነም፤ሀገራችን ጠብቀናል ከኃላ አልወጋናትም ሆኖም አሁን ህዝብን ከጨፈጨፉ ህዝባችን በይፋ የሚያውቃቸው በደሎች የፈፀሙ ቡድኖች እየተሸለሙ ሀገራችን በመስዕዋትነት በመጠበቃችን ከዕኩይ ሀይሎች ጋር ጥምረት የፈጠረው ስርዓት ህዝባችን ላይ በክህደት ጦርነት ከፍቶብናል።

መላው የሀገሬ ህዝብ ነገ የሚቆጭህ ነገር ከመከሰቱ በፊት በነቂስ ከጎናችን እንድትሰለፍ ጥሪ እናደርጋለን።

ጀግናው የፋኖ አዛዥ አርበኛ መሳፍንት ተስፉ

አንድነት ሀይል ነው!!

©የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር