በአዲስ አበባ የአማራ ተወላጅ መምህራን ለማፈስ አዝማሚያዎች ስለመኖራቸው ተገለጸ።

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)

ሚያዚያ 26/2015 ዓ/ም

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በአዲስ አበባ ከተማ በግልና በመንግስት ት/ቤቶች የሚያስተምሩ የአማራ ተወላጆች መምህራን ለማፈን የተዘጋጀ ሰነድ ፅናት ሚዲያ እጅ መግባቱ ተገልጧል።

መምህራን ለትምህርት ጥራት ተብሎ በአዲስ አበባ ት/ቢሮ የወጣ የኦህዴድ ሰነድ ሙሉ ለሙሉ ፖለቲካዊ ነው የሚሉት መምህራን አንኳር ጥያቄ ያነሱ ሰዎችን ለማሰር እንደተፈለገ ታውቋል ብለዋል።

አማራ ክልል ያለው ጦርነትን የሚደግፉ እነማን ናቸው የሚለውን ለመለየት እና አሸማቆ ለማሰር የተፈለገ ሰነድ መሆኑን መምህራኖች ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ሁሉም የመንግስት እና የግል መምህራን ከሚያዝያ 20-23 /2015 ስብሰባ ላይ የቆዩ ቢሆንም ከባድ ጥያቄዎች ከመምህራኑ ቢነሳም ያለ አጥጋቢ መልስ መበተኑ ይታወቃል።

ስብሰባ ከመጀመሩ ከአንድ ቀን በፊት ለኦሮሞ ተወላጆች ስብሰባ ላይ የሚያነሷቸው ነጥቦች ተነግሯቸው ነበር የሚሉት ምንጮች የአማራ ተወላጆችን ስሜታዊ እሚያደርጉ ነገሮች በማንሳት የሚቃወሙት በመለየት ሲንቀሳቀሱ ተስተውሏል።

ከጥያቄዎቹም ለአብነት

1.የአማራ ልዩ ሀይል ለምን ትጥቅ አይፈታም?

2.የአማራ ልጆች ፅንፈኛ ናቸው ብልፅግናን ይቃወማሉ።

3.የድሮ መንግስታት ልብስ ይለብሳሉ ለምሳሌ የምኒልክን እና የፋኖን፣

4.የኦሮሞ ባንዲራ ለምን አይሰቀልም? መዝሙር ለምን አይዘመርም?

5.አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት የሚሉ ሃሳቦች አንስተዋል።

በዚህም ጠንከር ያለ ትችት ያቀረቡ መምህራን ለማፈስ እንደተፈለገ ከመምህራን እማኞች ፅናት ሚዲያ መረጃዉን ማረጋገጥ ተችሏል።

የአማራ ሕዝብ የህልውና ጥያቄ ያስጨነቀው የኦህዴድ መንግስት በሁሉም ዘርፍ ያለ የአማራ ማሕበረሰብ ለማጥቃት በዘመቻ መልክ እንደተነሳ ማሳያ ሆኗል ይላሉ መምህራን።

ምንጭ-ጽናት ሚዲያ