May be a doodle of text

addisadmassnews.com 

 · ከአሽከርነትና ሎሌነት ወደ ነጻነት የሚደረግ ጉዞ!

የሰው ልጅ “ከጫካው ሕግ” ጀምሮ ያደረገው ዝግመታዊ የነጻነት ጉዞ እጅጉን አስደናቂ ቢሆንም፥ በዚህ ጉዞ ላይ እኛ ኢትዮጵያውያን ያሳረፍነው ሱታፌ ግን እጅግ ኢምንት ይመስለኛል። ለባሕርያችን የማይስማማውን አሽከርነትንም ለምደነዋል። አቢሲኒካ መዝገበ ቃላት አሽከርነትን፥ “ታዛዥ፣ ሎሌ፣ ተከታይ፣ አንጣፊ፣ ጋራጅ አስታጣቢ፣ አልባሽ፣ መጫሚያ አቀባይ፣ ዠርባ ጠቋሚ…ሳህን አመላላሽ” ይለዋል። ፕሮፌሰር ምንዳርአለው ዘውዴ ደግሞ፤ የዘመኑን የልሂቃን አሽከርነትና ሎሌነት፥ “ስናዳራዊነት” በሚል የሚመጥን ጸያፍ ቃል ይገልጸዋል። ስናዳሪ ማለት “ነፍሱን ለከርሱ፣ ህሊናውን ለኪሱ፣ ነጻነቱንና ክብሩን ለዕለት ጉርሱ የሸጠ ኑባሬ ነው” ሲል ከሰው ተፈጥሮ አሳንሶ እንስሳዊ ጠባይ ያጎናጽፈዋል።

ነጻነት እኩልነትና ወንድማማችነት

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በበኩላቸው፥ “አሽከርነት ባሕላችን ነው… ማሰብ የጌታው ተግባር እንጅ የአሽከሩ አይደለም…ጌታው ካላሰበለት በቀር አሽከር ነጻነት ስለሌለው አያስብም” ይላሉ። አሽከሮችና ሎሌዎች ዘንድ እውነት የሚፈተንበት አመክንዮ(Logic) እና አስተውሎት (Rationality) ስለሌሉ፥ እውነት የሚባለው የህሊና ፍሬ የላቸውም፤ የሙሉ ጊዜ ሥራቸውም አለቃቸውን ማስደሰትና ስለ እርሱ የውዳሴ ተረት መተረክ ነው። አሽከርነት ሥነ ኑባሬያዊ ደኅንነቱን (Onthological Security) ያጣ፣ ከሞቱት በታች ከሚኖሩት በላይ የሆነ፣ ኅሊና የሌለው፣ ደመ ነፍሳዊ እንስሳ ነው ማለትም ይቻላል። አሽከር ስለ ነጻነትና ስለ እውነት ሊያስብ የማይችል፣ ኢ-ሰዋዊ ጠባይ ነው።

በክርስትና ነገረ መለኮት ትምህርት ውስጥ፥ የሰው ልጅ በአምላክ አምሳልና አርአያ የተፈጠረ የአምላክ ባሕርያት ያሉት፣ ልዕለ ፍጡር እንደሆነ ይናገራል። የሰው ልጅ በነጻ ከአምላክ በጸጋ ከተሰጡት ባሕርያት ውስጥ አንዱ ደግሞ ነጻነት (freedom) ስለሆነ በነጻነት የማሰብ፣ በነጻነት የመንቀሳቀስ፣ በነጻነት የመሥራት፣ በነጻነት የመኖር መብት፣ ማንም በበጎ ፈቃድ የማይሰጠው አንዱ የክርስትና መገለጫ እንደሆነ ይናገራል። ዳሩ ግን የሰው ልጆች ለዘመናት የአምባገነን ባለሥልጣንና የባለሀብቶች አሽከር ሆነው፣ ሺህ የሰቆቃ ዘመናትን አሳልፈዋል። አሽከርነት የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ባህሪ ሳይሆን፣ የሰው ልጆች አምላክ የሰጣቸውን እምቅ የግል ሀብት በስንፍናቸው ምክንያት ሳይጠቀሙ ሲቀሩና ለሌሎች በፈቃዳቸው አሳልፈው ሲሰጡ የሚፈጠር የቁም ሞት ነው።

በጥንታውያን የነገሥታት ዘመን፣ የንጉሥና የባላባት አሽከር- ሎሌ መሆን ክብር ነበር። አሽከሮችና ሎሌዎች በክብርና በኩራት፣ “እኔ የንጉሥ እከሌ፣ የባላምበራስ እገሌ አሽከር ነኝ” እያሉ ይፎክሩ ነበር። ለሌላ አምባገነን ባለሥልጣንና ባለሀብት ታዛዥነትን፣ አገልጋይነትን፣ ባርነትን እንደ ትልቅ ክብር ቆጥሮ፣ የራስን ክብርና ነጻነት ነፍጎ፣ በሌላ ሰው ማንነት ውስጥ ራስን ማስጨነቅ፣ የሰው ልጆች ትልቁ ስቃይ ነው። የሰው ልጆች ይህንን መራራ ስቃይ ሲቀበሉ ኖረዋል፤ አሁንም በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፣ በዚህ የአሽከርነትና የሎሌነት ኢ-ሰዋዊ የሥነ ልቦና ማንነት የሚሰቃዩ እጅግ ብዙ ናቸው። አንዳንዶች ይኸንን የአሽከርነት ማንነት በጸጋ ተቀብለው፣ ማሰቢያ ኅሊናቸውን በፕሮፓጋንዳ ደፍነው፣ እንደ ኤሳው የሰውነት ብኩርናቸውን በምስር ወጥ ለውጠው፣ በአደባባይ ሳያፍሩ ለግፈኞች ሲያሸረግዱ ታይተዋል። እንደ ሊጋባው በየነ ያሉ ዘመን ያበቀላቸው ክስተቶች ደግሞ “ሀገሬንና ሕዝቤን እንጂ ከግፈኞች ጋር ኅብረት የለኝም” በማለት ሥልጣንን፣ ያማረ የንጉሣውያን የተዋበ ልብስን፣ የቤተ መንግሥት ጠጅና ጮማን እየናቀ፣ ከኅሊናው ጋር ቀዝቃዛውን እስር ቤት ይመርጣል። ሀገር በጣሊያን ተደፈረች ባሉት ጊዜ ግን ከእስር ቤት ወጥቶ፣ መትረጌሱን እንደ ቸኩቬራ ተሸክሞ በሰሜን የትግራይ ተራራ ሲዋጋ፣ ከንጹህ ኅሊናው ጋር ለኢትዮጵያ ሰማእትነትን ተቀበለ። ለኢትዮጵያ የሚጠቅማት እንደ ሊጋባው በየነ ያሉ ነጻነታቸውን በሆዳቸው ያልቀየሩ፣ ጀግኖች እንጂ የንጉሡ አሸርጋጆች አይደሉም።

ከ2000 ዓመታት በፊት የጽርዕ (የግሪክ) ፈላስፎች፣ የሰው ልጅ አርነት ይወጣ ዘንድ ቆም ብለው በኅሊናቸው አሰላስለው የተፈላሰፉበት “ያ” ነጻነት፥ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ደግሞ እንግሊዛውያን “የሰው ልጅ ነጻ ፍጡር ነውና በነጻነት ይኖር ዘንድ ይገበዋል” በማለት ከፍተኛ ንቅናቄ በመፍጠር፣ የማግና ካርታ ስምምነት አደረጉ። ከማግና ካርታ ስምምነት መካከል “ማንም ዜጋ ከሕግ ውጭ ሊታሰር፣ ንብረቱን ሊያጣ፣ ሕይወቱን ሊያጣ ሊሰደድ አይገባውም፥ ፍትሕንና መብትን ለማንም አንሸጥም” በማለት የነጻነት ነጋሪት ለሰው ልጆች ሁሉ ጎሰሙ። (“መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” ፤ገጽ 29) እንግሊዛውያን የዛሬ 800 ዓመት የጠየቁትን ጥያቄና በሕግ የደነገጉትን የሰው ልጅ የነጻነት መብት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዓለም እጅጉን በተራቀቀበት በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን፣ አይደለም ሊጠቀምበት ይቅርና ለመጠየቅ አለማሰቡ አስደንጋጭ ነው። የእንግሊዝ ሕዝብ የዛሬ 800 ዓመት የጠየቀውንና የተገበረውን የነጻነት መብት ለምን የኢትዮጵያ ሕዝብ መጠቀሙ ቀርቶበት ለምን ለመጠየቅ እንኳን አላሰበም? አንድ ኢትዮጵያዊ ይህንን የነጻነት መብት ለማግኘት ከሀገሩ ተሰዶ የግድ አሜሪካ መሄድ አለበት ወይ? አንጻራዊ የግለሰብና የማኅበረሰብ በነጻነት የማሰብ፣ የመንቀሳቀስና የመሥራት መብት እስካልተሰጠ ድረስ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማምጣት የህልም ቅዠት ነው።

አሁን አሁንማ ኢትዮጵያ ውስጥ አሽከርነትና ሎሌነት የማይገኝ አዋጭ የኑሮ ዘይቤ እየሆነ ነው። አሽከርነት የማይገኝ ቅንጦት እየሆነ መምጣቱ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያንም በኋላቀሩ በጥንታዊው የሰው ልጅ የማኅበረሰብ ሥርዓት ውስጥ ተቸክላ እንደቆመች አንዱ ማሳያ የመደብና የጎሣ፣ የገዥና የተገዥ፣ የጌታና የባሪያ፣ የንጉሥና የአሽከር ሥርዓት መቀጠሉ ነው። ሎሌነትንና አሽከርነትን አይደለም ከዜጎቻችው ላይ ይቅርና ከውጭ አገር ዜጋ ላይ ያነሱና ነጻነትን ያወጁ አገራት በኢኮኖሚ ከፍታ ላይ ይገኛሉ። አሜሪካ እ.ኤ.አ በ1976 ዓ.ም፤ “የሰው ልጆችና የዜጎችን አዋጅ” ስላወጀችና ስለተገበረች ለሰው ልጆች ሁሉ በንጽጽር ምቹ ሁኔታን ስለፈጠረች ምሑራን ከዓለም ዙሪያ እየተሰበሰቡ አሳድገዋታል። አንድ እውቅ ኢትዮጵያዊ የፊዚክስ ባለሙያ አሜሪካን ቢሄድ፣ በንጽጽር ከሀገሩ ኢትዮጵያ ይልቅ ባእድ በምትባለው አሜሪካ የተሻለ ነጻነት፣ ክብርና ክፍያ ካገኘ በዘመናት ያካበተውን እውቀት ለአሜሪካ ያለስስት የማይሰጥበት ምክንያት ምንድነው? በግልጽ አሽከርነት ውስጥ ግን ሳይንሳዊ ምርምርም ሆነ ጥልቅ ወገናዊ አሳቢነት አይኖርም።

የፈረንሳይ አብዮት የነጻነት ትሩፋት እንደ ማሳያ ተጨማሪ ያንብቡ

https://bit.ly/3p13mbk