May 6, 2023 

ሰውነቴ ይቅደም ወይስ ኦሮሞነቴ?!( ጎዳና ያዕቆብ ) 

————————//——————-

የኦሮሞ ብሔርተኞች ከኦሮሞ ተወላጆች እየጠየቁ ያሉት ሰብዓዊነት በጨካንነት…ሰውነትን ህፃናትን እና ነብሰ ጡርን እንኳን በማይምር ጭካኔ…ሀይማኖትን በፓለቲካል (ማኀበረሰባዊ ሳይሆን) ኦሮሞነት ለውጥ የሚል ውድ እና ልከፍለው ህሊና የማይፈቅደው…ሰውነት የማይፈቅደው ዋጋ ነው እየጠየቁ ያሉት::

በጭካኔ አንገቱን ለሚያርዱት የአማራ ማኀበረሰብ መጮህ ትተህ አራጅ በመባሉ አንገቱን ለሚደፋው ወግን እያሉ ነው:: ያን ማድረግ ፈፅሞ አይቻለንም!!!

ሰውነቴ አይፈቅድልኝም!!!

እኔ በመጀመሪያ በተፈጥሮ ማንነቴ ሰው…በዜግነት ማንነቴ ኢትዮጵያዊ…በብሔረሰባዊ ማንነቴ ደግሞ ኦሮሞ. ከኦሮሞም ቦረና ነኝ!!!

ስለዚህም እንደሰው የአማራው መከራ ይመለከተኛል…! ግድም ይለኛል…! እንደ ኢትዮጵያዊ በማንኛውም ኢትዮጵያዊ ላይ የሚደርስ ጥቃት እና መከራን በራሴ ላይ የተፈፀመ ያህል ያመኛል…! ግድም ይለኛል…! እንደ ኦሮሞ በስሜ የሚፈፀም ጭካኔ እና ግፍ ያመኛል…! ያሳፍረኛል…! አንገቴንም ያስደፋኛል…!

የተገኘሁበት ማኀበረሰብ ደግ ነው ሲባል እየተሰማኝ ያደግኩትን የልብ ኩራት ለልጅ..ለልጅ ልጅ ለማውረስ በስሜ የሚፈፀመው ኢ-ሰብዓዊ ብቻ ሳይሆን እንስሳዊ ድርጊት አምርሬ እቃወማለሁ…!

የተገኘሁበትን እና የምወደውን የማኀበረሰቤን መልካም ስም ለማደስ እታገላለሁ!!!

ስለዚህም ትግሌ እንደ ሰው…እንደ ኢትዮጵያዊና እንደ ኦሮሞ ነው!!!

የኦሮሞ ብሔርተኞች አስረግጠው ማወቅ ያለባቸው ነገር ቢኖር የነአብይ አህመድ አውሬነት ኦሮሞን የሚወክል ከሆነ እኔ ሰው እንጂ አውሬ አይደለሁምና ስለ ኦሮሞነቴ ለማሰብ እገደዳለሁ!!!

ስለዚህም ጥያቄዬ አንድ እሱም እነ አብይ አህመድ ሲፈፅሙት የኖሩትና እየፈፀሙ ያሉት አረመኔአዊ ድርጊት የኦሮሞነት መገለጫ ነው ወይስ አይደለም?!