Mengistu Musie
· የፕሪቶርያ ስምምነት የሁለት ኢህአዴጎች የመልሶ ጋብቻ
=================
ዘረኞቹ ህወሓት/ኦነግ ብልጽግና ያደረጉት ስምምነት የእንደገና alliance against their strategic enemy and resistance to a radical socioeconomic change ነው እንጅ ዘላቂ ሰላም እና ዴሞክራሲያዊ መንግስት የማስፈን አላማ የለውም።
ሰሞኑን ከሰሜን አሜሪካ የህወሓት ሚዲያወች እስከ የህወሓት ዲጅታል ካድሬወች መጠነ ሰፊ ፕሮፖጋንዳ የአብይ አህመድ መንግስትን በሚቃወሙት ላይ ከፍተዋል። ገራሚው ከዚህ በፊት ህወሓትን እንቃወማለን በሚል ዩቱብ ከፍተውም ጦርነቱን የደገፉት የትግራይ አድርባዮች ሳይቀር ይህን የኦነጋዊውን መንግስት ተቃዋሚወችን ማክቸልቸል ጀምረዋል።
ግልጽ የሆነው የነዚህ ሚዲያወች እና ዩቲውብ ሰወች አላማ እንደሚያሳየው አሁንም ለዘላቂ ሰላም መሰረታዊውን የስርአት ችግር ለመፍታት በቀጠናው በዘር ፖለቲካ እና ህገመንግስቱ የተነሳ ተቃውሞ ያነሱ ወገኖችን እና ጦርነቱ የለበለባቸውን ቀጠናወች እና ሕዝብን ዘላቂ የሆነ የሰላም ጥሪ ወይንም ስለሰላም ከመስበክ ጦረኞቹ ትናንትም ሆነ ዛሬ ጦር የሰበቁት ኢሕአዴጎች ለሁለት ተከፍለው በስልጣን መሆኑን እረስተው ወይንም ያነን ወደጎን አርገው አሁንም የጥላቻ ፕሮፖጋንዳቸውን በአማራ (በህገመንግስታቸው ጠላት ብለው በፈረጁት) ሕዝብ ላይ እና በጎረቤት እና አካባቢ ሕዝቦች ላይ አነጣጥረው መስራት ጀምረዋል።
ድጋሜ እንመክራለን– ይህ የታክቲክ ለውጥ ለዘላቂ ሰላም ሳይሆን ለባሰ የሕዝባችን ህይወት ቀጣፊ እና አውዳሚ መሆኑን ተገንዘቡ እንላለን። ዛሬ ህወሓት/ኦነግብልጽግና የያዙት ስልት ሰላም የሚያመጣ ሳይሆን ያነኑ ያየነውን በሁለተኛው የአለም ጦርነት 72 ሚሊዮን ህይወት ከቀሰፈው የበለጠ መሆኑን በስታትስቲክስ ማሳየት ይቻላል። በሁለተኛው ያለም ጦርነት ጦርነቱ መላ አለምን ያነካካ ሲሆን በዋናነት ሙሉ አውሮፓን ሶቪየት ህብረትን እና አሜሪካንን ያካተተ ጦርነት ሲሆን የጠፋው ነፍስ ከ 72 ሚሊዮን እስከ 85 ሚሊዮን ይደርሳል። በሰላማዊ አለም በአንድ ሐገር ውስጥ በተካሄደ የሁለት አመት የዘር ፖለቲካ በፈጠረው ይዋጣልን በሚል የተደረገው ፍጅት ከዚያ አለምን ካካተተ ጦርነት የሚያንስ አልነበረም።
ይህን ጦርነት ቀስቃሾች እና ሁለቱ ኢሕአዴጎች ዛሬም ስህተታቸውን አይተው ተጸጽተው ሳይሆን ሌላ ዙር የእርስ በእርስ ግጥሚያን ሌላ አልያንስ ፈጥረው ለማድረግ መከጀላቸውን ከጀመሩት የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ እና ዛቻ መረዳት ይቻላል።
እስታሊን ገብረስላሴ የተባለ ልምዱም እውቀቱም የጎደለው የህወሓት የሚዲያ ሰው ያጦርነት በተነሳበት ሰሞን “የኔ ትውልድ ኢትዮጵያን ስትፈርስ በአይኑ በማየቱ እኮራለሁ” እንዳላለ ዛሬ ለሚሊዮኖች ትግራውያን እና አፋሮች እና አማሮች አጥፊ የሆነውን ጦርነት በቀሰቀሰበት አንደበት ተገልብጦ ተመሳሳይ መንግስትን የሚደግፍ ቅስቀሳ እና ሌሎችን የሚያጥላላ ሲያካሂድ ማየት በእርግጥ ከህወሓት ጽህፈት ቤት የተሰጠው መመሪያ መሆኑን ሳንስት ይህ በቀቀን ዛሬም የጥፋት መርዙን በተከፈለለት ሚዲያ ማስተጋባት መጀመሩን ሳይ ከምር ማዘን እና ዘረኝነት እራስን መቃቭብር ሳይከት የማይለቅ በሽታነቱን አስረድቶኛል።
ግን ችግሩ የሞሶሎኒ እና የሂትለር ዘረኝነት ምንም እንኳን እራሱን ቢበላም ሚሊዮኖችን አጥፍቶ የጠፋ መሆኑ መዘንጋት የለበትም እና በእኛም ሐገር 1967 ተወልዶ 1991 ለስልጣን በቅቶ እንደገና ቁልቁል ቢሄድም ውላጁ ሰፊ ጉዳት የሚያደርስ እንደሆነ ተገንዝቦ ሕዝብ ይህችን ሐገር እና ይህን ሕዝብ ነጻ ሆኖ እንዲኖር መስዋእት የሚፈልግ ትግል ይጠብቀዋል።All reactions:44