May 9, 2023 

በምስራቅ ወለጋ ዞን በአንገር ጉትን ከተማ በሰሞኑ ባገረሸው እስራት የከተማዋ ኗሪዎች ተረጋግተው ለመኖር አለመቻላቸውን ተናገሩ።

አሻራ ሚዲያ

በምስራቅ ወለጋ ዞን በአንገር ጉትን ከተማ በሰሞኑ በጉትን ተኩስ የሚጀመረው በተውፊቅ መስጊድ አካባቢ ሲሆን ከተጀመረ በኋለ በየ አቅጣጫው ነው የሚተኮሰው ፤ የሚሉት ነዋሪዎቹ ከትናንት በስቲያ ያያቸው ሰው አልነበረም። ትናንት ግን በትክክል ታይተዋል ሲሉ ተናግረዋል። ከመስጊድ ዝቅ ብሎ የኳስ ሜዳ አካባቢ ተኩሱን ጀምረው ከሰዓታት በኋላ በየአቅጣጫው ሲተኮስ አደረ ብለዋል።

ዛሬ ደግሞ ሁለት ንፁሃን የከተማዋ ኗሪ የሆኑት ለእስር ተዳርገዋል። ከነዚህም መካከል፦

1- ሙሀመድ ሰይድ የሚባል እና
2- ሙሀመድ አህመድ የሚባሉ በፖሊስ እና በሚኒሻ ወስደው አስረዋቸዋል።