May 10, 2023 – Getachew Shiferaw 

መሸፋፈን አያስፈልግም!

1) እነ ሽመልስ አብዲሳ በቀጥተኛ ትዕዛዝ አዲስ አበባ ላይ እያመጡ እንደሚያስገቡት ካድሬ፣ ተሃድሶውንም፣ የሀሰት ነብዩንም፣ አባገዳውንም፣ ያኮረፉትን የኃይማኖት አባቶችንም አደራጅተው “ሲኖዶሱ ይሹምልን” ብለዋል። ሲኖዶሱ የሚሾመው በእምነቱ መሰረት እንጅ በፖለቲካ አይደለም ተብለዋል። ካልሆነ ሲኖዶሱ ይፈርሳል እያሉ እየዛቱ ነው። የመንፈስ ቅዱስን ተግባር የካድሬ ምደባ አድርገውታል።

2) ትህነግ በድሮን ሲቀጠቅጠው ከነበረው ጋር ታርቆ፣ የትግራይ አባቶች ግን ቤተ ክርስትያንን እየወቀሱ ነው። ጌታቸው ረዳ ከአብይ አህመድ ጋር እየዋለ የትግራይ አባቶች ሲኖዶሱን ለጦርነት ተጠያቂ አድርጓል። ይህ እየሆነ ያለው ትህነግ በቤተ ክርስትያን አባቶች በኩል ጩኸቱን ማስቀጠል ስለፈለገ ነው። የሚያሳዝነው ደግሞ እነዚህ አባቶች ከትግራይ ውጭ ጦርነት የነበረ አይመስላቸውም። መነኩሴ የደፈረው፣ ቄስ የገደለው ትህነግ ለእነሱ ቅዱስ ነው።

3) ባለፈው የተወገዘው ቡድን ጋር በነበረው ችግር የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት በጌታቸው ረዳ እና ታደሰ ወረደ በኩል “የትግራይ አባቶችም የራሳቸውን ቤተ ክርስትያን ያቋቁሙና የ”ብሔር ብሔረሰብ ሲኖዶስን ያግዙ” ተብሎ ተሰርቶበታል። አሁን ሁለቱ ተገንጣይ ሲኖዶስ ሆነው ሹመትና ይቅርታ እየጠነቁ ነው።

4) በጣም በሚከረፋ ሁኔታ በእምነት ስም ጥላቻው ህዝብ ላይ ነው። “በአማርኛ ቋንቋ ስብከት”፣ “ከጎጃምና ጎንደር እየተመደቡ” እየተባለ በሀሰት ጥላቻ የሚነዛው ህዝብ ላይ ነው።

ቤተ ክርስቲያን ከባለፈው የከፉ አደጋ ተደቅኖባታል። የሲኖዶሱ መግለጫ በርካታ ህመምን አጭቆ የያዘ ነው። እውነታው ቤተ ክርስቲያን በግድ ተገንጣይ ሹሚ ተብላ ትዕዛዝ መጥቶባት፣ አይሆንም ብላለች። ችግሩ ግን ቀላል አይደለም።