በ2022 ኢትዮጵያ በተፈናቃዮች ብዛት ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን በማስቀደም በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የኖርዌ የስደተኞች ካውንስል የተፈናቃዮች ክትትል ማዕከል አስታወቀ፡፡
ማዕከሉ ይፋ ያደረገው የ2022 አመታዊ መረጃ እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ አጠቃላይ ተፈናቃዮች ቁጥር ሁለት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አምስት ሺ መሆኑን አስታውቋል። ከዚህ ውስጥ ሁለት ሚሊዮን 32 ሺ የሚሆኑት የተፈናቀሉት በግጭት እና ብጥብጥ ምክኒያት መሆኑም ተገልጧል፡፡
በኢትዮጵያ በድርቅ ሳቢያ ብቻ በ2022 ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 686ሺ መሆኑን የጠቆመው ማዕከሉ በተለይም በኦሮምያ እና ሶማሌ ክልሎች ሁኔታው የከፋ መሆኑን አስታውቋል፤ በሁለቱ ክልሎች ከድርቁ በተጨማሪ ግጭት እና ሁከት ጉዳት እንዳደረሰባቸው አመላክቷል።
@ addis standard
