·
ኢሮብ እቺ ናት!
(Re-Posted)
ኢሮብ በትግራይ ክፍለ ሀገር፣ ዐጋመ አውራጃ (ምሥራቃዊ ዞን) ውስጥ የምትገኝ ወረዳ ናት! ተራራማ መልክዐ – ምድር ያላት ስትሆን በትግራይ ክልል ከሚገኙት 3 ብሔረሰቦች አንዱ በሆነው የኢሮብ ብሄረሰብ ይኖርባታል፡፡
ኢሮብ – የወረዳውም፤ የብሔረሰቡም መጠሪያ አንድ ነው፡፡ ኢሮቦች ሳሆኛ ተናጋሪ ናቸው! ኢሮቦች የሚናገሩት ቋንቋ በኤርትራ ምድር ከሚነገረው የሳሆ ቋንቋ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ሆኖም በኤርተራ የሚገኙ የሳሆ ተናጋሪች ብሄረሰብ ሳሆ ተብሎ የማጠሩ ሲሆን ኢሮብ እና ሳሆ በኢኮኖሚ ስምሪታቸው ይለያያሉ፡፡ የሳሆ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ አርብቶ አደር ነው፡፡ ኢሮቦች ግን በአርብቶአደር፣ በእርሻ ሥራ፣ በአነስተኛ ዕደ-ጥበባት ይተዳደራሉ፡፡ ከኮንሶ እርከን ጋር ይዛመዳል፡፡
የኢሮብ ወረዳ ተራራና ሸንተረር ይበዛዋል፡፡ በአካባቢው ካሉት ተራሮች መካከል ‹‹አሲምባ – በኢሕአፓ የትጥቅ ትግል የሚወሳ››፣ ‹‹አይጋ – የኢትዮ- ኤርትራ ከባድ ውጊያ የተደረገበትና ታሪክ የሰነቁ ተራራዎች ናቸው፡፡ አሊቴና – ከተማ የኢሕአፓ የትጥቅ ትግል ሲካሄድበት የነበረው የአሲንባ ተራራና የአይጋ ተራራ መገኛ ናት፡፡ በዚህች ከተማ ከኢሕአፓ መሥራቾች አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ተወልዷል፡፡ ኢህአፓዎች ከማንም በላይ የሚያከብሩትና የሚያደንቁት አርበኛና የለውጥ ብስራት ነጋሪ ፋኖ! የጽናትና የቆራጥነት ተምሳሌት ሆኖ በየዓመቱ የሚዘከር የዚያ ትውልድ ታላቅ ሰው – ዶክተር ተስፋዬ ደበሳይ!
የአሲንባ ፍቅር ገጽ 53-56 ከተጠቀሱት ውስጥ ይህቺን ልቀንጭብላችሁ … “የኢሮብ ሕዝብ ውጊያ የማይፈራ፤ ያገኘውን ተካፍሎ የሚበላ፤ ያመነውን በፍፁም አሳልፎ የማይሰጥ፤ እስከተፈለገው ጊዜ ደብቆና ጠብቆ የሚያቆይ፤ ህዝብ ነው፡፤ የኢሮብ ሕዝብ ካመነ አመነ ነው፡፡”
ኢሮብ- መልካም፣ ቅን፣ ትሁት፣ ወዳጅ ፣ ፍቅር ፣ ሩህሩህ፣ ለጋሽ ፣ አስተዋይ የሆነ ህዝብ ይኖርባታል። በሕዝብ ደረጃ ጥልና መከፋፋት የለም። የኢሮብ ህዝብ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው፡ ሀገሩን የሚወድ፣ እጅግ ሃይለኛ ጦርነት ገጥሞ የማያፈገፍግ ምርጥ ተዋጊ፣ ቸር ተባባሪ እና እንግዳ አክባሪ ህዝብ ነው። ለዳር ድንበሩ ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከስክሶ ኢትዮጵያን ዛሬም ደምህ ደሜ ነው እያለ ፍቅሩን እየገለጠ የሚገኝ ጀግና ፣ እንግዳ ኣክባሪ ና የዋህ የሆነ ህዝብ ነው። የኢሮቦች የመተማመንና የመረዳዳት ባህል ደግሞ ሁሌም አስደናቂ ነው፡፡ ግእዝም የተባለው ባሕላዊ ምግባቸው ግን በጭራሽ ሳይጠቀስ መታለፍ የለበትም፡፡
ኢሮቦች – ድሞክራስ (democracy) በዓለም በስም እንጅ በተግባር ያልነበረ ግዜ በድሞክራስያዊ አካሄድ ስመርጥና ስመራ የነበረ ህዝብ በመሆኑ ለአገራችን ድሞክራስያዊ ሰርዓት ግንባታ ተምሳሌት መሆን የምችል ህዝብ ነው።
ኢሮብ የሚታወቀው አንድ የነዋሪው ልማዳዊና ባህላዊ ጠባይ፣ መቻል፣ መታገሥና ሁሉን እኩል በማስተናገድ ነው፡፡
ህንፃም ልጅ ቢሆን፡፡ በሠርግ ወቅት የሚታደል ማንኛውም ነገር እንኳ ለልጅም እኩል ይደርሳል፡፡ ከተማይቱ ለጦርነት አመቺ ከሆኑት እንደ አሲምባ ተራራ እና አይጋ (ሻቢያ በጣም የተመታበት ቦታ) አሊቴና (ዳውሃን) ዓይነት ቦታዎች አካባቢ በመሆንዋ የደርግ ጦር፣ የኢዲዩ ጦር፣ የኢህአፓ ጦር፣ የህወሓት ጦር፣ አንዳንዴም የህዝባዊ ግንባር ጦር ወዘተ ኃይሎች እንደመተላለፊያ በየጊዜው እየመጡ ይሰፍሩባት ነበር፡፡ ህዝቡ እነዚህን ኃይሎች በአግባቡ፣ ሳያጋጭና ሳያጣላ፤ አንዱን በፊት ለፊት አንዱን በጀርባ/ በጓሮ አስተናግዶ ኮሽ ሳይልበት ይሸኛቸዋል፡፡ ለኢሮብ ውይይት ዋና ባህል ነው፡፡ ህዝቡ የአገር ሽማግሌ ይኖረዋል፡፡ የእድር ዳኛ፣ የማህበር መሪ፣ የጎበዝ አለቃ ወዘተ እንደሚባለው ዓይነት የበሰሉ፣ ብልህነት የተዋጣላቸውና ህዝቡ እህ ብሎ የሚያዳምጣቸው አባት (አቦይ) ይኖሩታል፡፡
ኢሮብ – አስደናቂ ጠቢባን ነገስታት እና ተወዳዳሪ የሌላቸው እልፍ አእላፍ ጀግኖች ማፍለቂያ ነው- ። የኩራታችን ምንጭ፣ መነሻን ነው ብባል ምንም ክፋት አይኖረውም፡፡
ኢሮብ – እጅግ የሚገርም ታሪካዊ አካባቢ ነው፡፡ ኢሮብ- “እምቢኝ” ለመብቴ ማለት የምችሉ ከህዝባቸው አልፈው ለሀገር የተረፉ ፍርጦች አፍላቂ ህዝብ ነው.! የኢሕአፓ መሪ የነበረው ዶክተር ተስፋዬ ደበሳይ: አንጋፋው ታጋይ በየነ ገብራይ: የቪኦኤ ጋዜጠኛ አዳነች ፍስሐዬ: አዲስ አበባ ላይ የተገደለው ጋይም ፤ ድምፃዊት ራሄል ሀይሌ ፤ ድምፃዊት የሺ ብርሐነ ድምፃዊ ተሰፋይ ግርማይ እነዚህ የኢሮብ
ልጆች ናቸው ።
ኢሮብ – የነደጃች ሱባጋዲስ (ማሸነፍን አበልፃጊ እንደማለት ነው) አገር ናት፡፡ የነኣጼ ቴዎድሮስ ባለቤት እቴጌ ጥሩወርቅ አገር ናት! (እቴጌ ጥሩወርቅ – የደጃት ስባጋድስ ወልዱ የልጅ ልጅ ናቸው።) ኢሮብ የነዐፄ ዮውሃንስ 4ኛ አገር ናት! ኢሮብ የነኃየሎም አርአያ አገር ናት! ኢሮብ የነኢሳይያስ ኣፈወርቂ አገር ናት (his wife is Irob from Daro)! ኢሮብ የነ መንገሻ ዮሐንስ አገር ናት! ኢሮብ የነራእሲ ስብሓት ኣረጋዊ (ኣባ ጠቕልል) አገር ናት! ኢሮብ የነሹም ዓጋመ ኣረጋዊ አገር ናት! ኢሮብ የነዶክተር ተስፋዬ ደበሳይ አገር ናት! ኢሮብ – አስቀድሞ ነገሮችን በመረዳት ስጦታቸው የሚታወሱት ፊተውራር ተሰማ አገር ናት! ኢሮብ የነሰለቃ ወልዱ ገብራይ፡ ኣባ ወልደማሪያም ካሕሳይ፡ ኣቡነ ዮሃንስ ወ/ገርግስ አቡና ተሰፋሰላሴ መድህንና አቡና አብርሃም ደሰታ አገር ናት!
ኢሮብ- ከረዣዥሞቹ ተራሮች ስር በድንቅ ጥበብ በድንጋይ የታነጹ፤ እንደ ላሊበላ ውቅር ዐለት ያልሆነ፤ እንደ ጎንደር፣ እንደ ሀረር እንደሌሎችም የማይመስል፤ የራሱ መልክ፣ የራሱ አሰራር፣ የራሱ ጥበብ የሚታይበት የደብረ ገሪዛን ጉንዳ ጉንዶ ማርያም ገዳም አገር ናት!
በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲን በመመስረት ቁልፍ ሚና የተጫወቱት ደጃዝማች አየለ ስብሐት፣ ከትግራይ ታዋቂ መኳንንት አንዱ የሆኑት ደጃዝማች ሱባጋድስ የጦር አለቃቸው ብላታ ፍሱሕ፣ በኢትዮጵያ ቀዳሚ ከሆኑት የዶክትሬት ዲግሪ ባለቤቶች አንዱ የሆኑት ዶ/ር አባ ሐጎስ ፍሱሕ፣ ፍትሐ ነገስት ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ የተረጎሙት አባ ተስፋስላሴ ወልደገሪማ፣ የአስተዳደር ሰው ቀኛዝማች ስዩም፣ የፓለቲካ ተመራማሪ – ፈላስፋና የዶ/ር ተስፋይ የቅርብ ወዳጅና ራሱ የግራ ክንፍ የፓለቲካ ሰው የነበረው ዶ/ር ተሰማ ብስራት ወዘተ. የፈለቁት ከኢሮብ ነው፡፡
ኢሮብ – የዘመናዊ ትምህርት ለሃገራችን ፈር ቀዳጅ ነው! የኢትዮጽያ የመጀመርያው ዘመናዊ ት/ቤት ኢሮብ ውስጥ እንደተከፈተ ስንቶቻችን እናውቃለን ? በ1837 ዓ·ም ዘመናዊ ትምህርት በዓሊተና – ኢሮብ- ተከፈተ! ቀጥሎ ጎልዓ- ቀጥሎ ዓድዋ! ከ60 “ዓመት በኋላ (1902) አዲሳበባ ተከፈተ ታሪኩ ይህ ነው። ይሰጥ የነበረው የትምህርት ዓይነትም ግእዝ፣ አማርኛ፣ ላቲን፣ ቲኦሎጂና ሥነ ቅርፅ ሲሆን፣ የማስተማሪያ ቋንቋው በአብዛኛው አማርኛ ነበረ፡፡ በአገራች መጀመሪያ ዘመናው ትምህርት የተጀመረውን በዓልተና – ኢሮብ ውስጥ ነው።
የዐጋመ ዘር ከኢሮብ መሆኑስ ስንቶቻችን እናውቃለን? ስለ ኢሮብ ቡዙ ማለት ይቻላል! ኢሮብ – የንጉሦች መሰረት የዓጋመ ኩራት ነው! ኢሮብ የሚወደድ ህዝብ ነው! የኢሮብ ይዞታ/ግዛት የቅርብ ጊዜውን ከወሰድነው፤ ሱቡሓ ሳዕስዕ (እስከ ኮማ ሱቡሓ-ዕዳጋ ሓሙስ አከባቢ) ፤ ሰራየ፤ ዓዲግራት እስከ ሙጉላት/እንትጮ ፤ ጉለመካዳ የተወሠነ ቦታዎችንና
የአሁኑዋን ኢሮብ ወረዳን ግዛት በሙሉ ያጠቃለለ ነበር። አሁንም ቢሆን እነ ሣውነ፤ ማርዋ ፤ጋብለን ፤ ሚርግዳ ፤ ፈረዳሹም…ወዘተ ሳሆኛ ተናጋሪ ኢሮቦች ናቸው!
** ወደ ኋላ ትንሽ ተጉዘን (15 ክ.ዘ ኣጋማሽ ድረስ) ካየነው ደግሞ የኢሮብ ይዞታ/ግዛት እስከ ፅራዕ- አፅቢ ወንበርታ፤ አጉላዕ፤ ደስዓ አከባቢ ድረስ ያጠቃልል ነበር…ወዘተ —— (ይሄንን በነገራችን ላይ አሁን እንኳ በደስዓ አከባቢ ያሉ ትላልቅ ሰዎች የሚውቁትና የሚመሰክሩት እውነታ ነው) ።
## ጥንተ መነሻችን በተመከለተና ደረጃ በደረጃ እንዴት በሌሎች እየተዋጠን (ASSIMILATED) ናእየጠፋ እንደመጣ ነው!
የኢሮብ ህዝብ ጀግንነት – ሻዕብያ በድንገት ሉኣላዊነታቸን በደፈረበት ወቅት ጀግናው የኢሮብ ህዝብ ከያለበት በመሰባሰብ ታንክና መድፍ ይዞ ለተንቀሳቀሰው የሻዕብያ መደበኛ ሰራዊት ገበሬው ምንም ዘመናዊ መሳርያ ሳይኖረው ወኔ ሰንቆ ወራሪውን ሀይል ባለበት እንዲቆም ተፋልመዋል ፡፡ በዚህም ለሉአላዊነቱ መስዋእት ከፍለዋል ጀግናው የኢሮብ ህዝብ ፡፡ በተለይም ዕጡቓት ሰንበት ተብለው የሚታወቁትን ፡ እሁድ ታጥቀው በነጋታው ሰኞ ዕለት ሻዕብያን ሲፋለሙ የዋሉበት ቀን ነበር ፡፡በዚህም ታሪክ ሰርተዋል ጀግኖቹ የኢሮብ ልጆች ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል!
“የሰንበት ታጣቂዎች” ወይም “ዕጡቓት ሰንበት” ተብለው የተሰየሙ የኢሮብ ማሕበረሰብ አባላት በኢትዮጵያና ኤርትራ በተካሄደው የመጀመርያ ጦርነት በደንበር አከባቢ መደበኛ ወታደር ባለመኖሩ ሻዕቢያ ዓይጋን ለመቆጣጠር ከዛም ከቀናው ግስጋሴውን ሊቀጥል ከጅሎ ጦሩ ስያዘምት በአከባቢው ምሊሻ ታጣቂዎች መስዋዕትነት እነሱ ሲወድቁ ደግሞ ልምድ የሌላቸው ልጆቻቸው ጠመንጃውን አንስተው በመታኮስ ሻዕቢያ ከባድ ኪሳራ ደርሶበት እንዲሸሽ እርምጃውም እንዲቀንስ አድርገዋል ። በሃላም ተደራጅቶ በከባድ መሳርያ በመታገዝ አከባቢውን በኢትዮጵያ መ/ሰ ነፃ እስኪወጣ ይዞት ነበር !
“ይህ አከባቢ በኢያዮ/ኤርትራ አውቀዋለሁ እና በዲያሪዬ ላይ እንዳሰፈርኩት ማስታወሻዬ አይነት ነው የዘገብከው። በህዳር ተህሳስ አባቢ ይመስለኛል 1991 ዓ.ም አከባቢው በጉም ይሸፈን እና ተራራዎቹ ሸናኖ እኛን እና ሻቢዎች ከቅርብ እይታ ይጋርደን ነበር። ብርዱ ታድያ አይወራም ። ከሁሉ በላይ ይደንቀኝ የነበረው ጥጥ የመሰለው ጉም እስከ አሲምባ ያሉት ተራሮችን ሸፍኖ ደሴቶች አስመስሏቸው ሲታይ፣ እኛ በተራሮቹ አናት ላይ ሆነን ወደ ጉሙ ታች ስንመለከት ባህር ላይ በደሴቶቹ በአንዱ ላይ ያለን ይመስለን ከጦርነቱ ጭንቀት ያወጣን ደስ የሚል ስሜት ይፈጥርብን ነበር።” – ዮውሃንስ ሞላ
More on Irobs!
1. Irob people are founders of EPRP movement,
2. Belles (edible fruits) is introduced to Ethiopia via Irob people and land
3. It is a region where the legendary Makeda (the Queen of Sheba) was born and raised.
4. Catholic religion was first introduced to Ethiopia via Irob people and land
5. Irobs were Leaders of Tigray-Tigregn for several decades
6. Second historic place for TPLF (woratle) after dedebit is located in Irob
7. Dej. Ayele Sebhat, also of Irob, played an important role in diplomatic and defense matters. It was he who was in forefront in establishing ambassadorial level relationship between Ethiopia and France and founded the Ethiopian embassy in Paris. He was also one of the most prominent patriots during the war of resistance against the Italians.
ኢሮብ ከዚበላይ ታርክ ያልው ህዝብ ነው። የምጽፍ ታጣ እንጅ!
ኢሮብ- ሰለስተ ኢሮብ – የጀግንነት መሰረት የዓጋመ ኩራት!
ጋዜጠኛ ጌጡ ተመሰገን