ቤታቸው የፈረሰባቸው ባል እና ሚስት በጥይት ተገደሉ።
በሰበታ ከተማ በኬንተሪ ደረቶ በሚባል ቦታ የአቶ መሀመድና የጎረቤቶቹ ቤቶች የፈረሱት ከትላንት በስቲያ ነበረ። ሙሉ ሰፈሩ ፈርሶ አልቋል ማለትም ይቻላል። አቶ መሀመድም እዛው ሰፈር ከገባ ወደ 18 አመት ሆኖታል።
ቤት ከፈረሰባቸው ሰዎች መሀከል የአቶ መሀመድ አብደላን ጨምሮ የሁለት ቤተሰብ አባላት ቤታቸዉ ከፈረሰባቸዉ በኋላ የሚሄዱበት አጥተው ተቸግረዋል። ትላንት ከሰአትም አብዛኛው እቃቸውን ወደ ገጠር ከጫኑ በኋላ ሰፈራቸዉ በሚገኝ አንድ ያላለቀ የሪልስቴት ፎቅ “ግራወንድ” ቦታ ያለ በመሆኑ በባለቤቱ መልካም ፍቃድ “ቤት እስክታገኙ እግቡ” ብለዋቸዉ ገቡ።
ማታ ፖሊሶች መጥተው እነመሀመድ የተኙበትን የህንፃውን “ግራወንድ” በር መደብደብ ጀመሩ። መሀመድም ማንነታቸውን ለማጣራት በመጠየቅ ላይ እያለ በሩ በሀይል ተሰበረ። በመቀጠልም አቶ መሀመድ አብደላ እንዲሁም ባለቤቱ ለቢባ ጀማል በጥይት ተመቱ ።
ጩኸቱን ሰምተው ከመጡት ጎረቤቶች መካከል አራስ የሆነችው ሉባባ ብላቱ በጥይት ተመታ ስትሞት ባለቤቷ ደግሞ ከቆሰለ በኋላ አምልጧል።
በጻውሎስ ሆስፒታል ያደረውን አስክሬን አሁን ተቀብለናል።
Tesfa G Neda – ከጳውሎስ ሆስፒታል
