ምርጫ ቦርድ ሕወሃት ሕጋዊ ሰውነቱ እንዲመለስለት ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን አስታውቋል።
ቦርዱ፣ ለውሳኔው ምክንያት የኾነው ኃይልን መሠረት ያደረገው የአመጻ ተግባር አኹን እንደሌለ ጠቅሶ፣ ኾኖም ሕወሃት ያቀረበው ሕጋዊ ሰውነት ጥያቄ የማስለስ ጉዳይ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 ላይ እንዳልተካተተና በሕግ የተደገፈ ኾኖ ስላላገኘው እንደኾነ ገልጧል።
ሕወሃት ሕጋዊ ፓርቲ መኾን የሚችለው፣ በድጋሚ የምዝገባ ጥያቄ ሲያቀርብና ቦርዱ ሲቀበለው ብቻ መሆኑን ቦርዱ አብራርቷል።
ሕወሃት በአባላቱና ንብረቶቹ ላይ የተጣለው እገዳ ጭምር እንዱነሳ ያቀረበውን ጥያቄም፣ ቦርዱ እንዳልተቀበለው ገልጧል።
ምርጫ ቦርድ የሕወሃትን ሕጋዊ ምዝገባ የሰረዘው፣ የሰሜኑ ጦርነት በተጀመረ ማግስት “ኃይልን መሠረት ባደረገ የአመጽ ተግባር ላይ ተሠማርቷል” በማለት ነበር።
