Neamin Zeleke
· ተጠያቂነትና ግልጽነት የሌላቸው የጠ/ሚንስትሩ የቤተ መንግስት ግንባታና፣ የቅንጦት ፕሮጄከቶች 850 ቢሊዮን ብር ($10 ቢሊዮን +) እንዲሰረዝ፣ የሚሊዮኖች ዜጎች መሰረታዊ ፍላጎት እንዲሟላ መሞገት፣ መታገል ያስፈልጋል።
ለውጭ መንግስታት፣ ተቋማት መሞገት፣ ማቅረብ አለብን። አገዛዙ 2 ቢሊዮን $ ከአለም ባንክ ብድር ይለምናል፣ በአንጻሩ ደግሞ በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ሚሊዮኖች በቂ ትኩረት አይሰጥም፣ በመቶ ሺዎች ያፈናቅላል፣ ለልመና ይዳርጋል፣ በየመጠለያው ያስርባል። በሌላ በኩል ደግሞ የ 10 ቢሊዮን ዶላር+ ቤተ መንግስት ግን ይገነባል። የዝቅጠት፣ የሰብእና የህሊና እውርነት ጥግ!
የውጭ ብድሮችና ኢኮኖሚያዊ እርዳታዎች ቅድመ ሁኔታ እንዲደረግ በውጭ የምንገኝ ሀገር ወዳዶች ሁሉ መታገል፣ መሟገት ወቅቱ የሚጠይቀው ሰላማዊ የትግል ስልቶች አንዱ ነው።የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄዎች– ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ ሰብአዊ መብቶች፣ፍትህ፣ የህግ የበላይነት- እንዲከበሩ እንዲረጋገጡ ተደራጅተን፣ ተናበን መሞገት መታገል አለብን።
የኢትዮጵያ ህዝብ መሰረታዊ ፍላጎቶች-መጠለያ፣ ምግብ፣ ንጹህ ወሃ፣ መብራት፣ ለመሰረት ልማት- የብድሮችና የእርዳታዎች ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሆኑ መታገል፣ መሟገት የትግሉ አካል ነው፣ በጠ/ሚኒስትሩ አይዞህ ባይነት በኦሮሞ ብልጽግና መሪ ካድሬዎች የሚዘወረው፣ ኢ-ሕገ-መንግስታዊነት፣ጋጠ ወጥነት፣ ምዝበራና ሙስና፣ ሰፊ አፈና እና ሰብአዊ መብቶች ረገጣ፣ ነቀላና ፍንቀላ በአግባቡ ተሰንዶ፣ ለመንግስታት ለአለም አቀፍ ተቋማት ማቅረብ።
ማናቸውንም ዘረኛና ግፈኛ፣ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ማስገደድ የሚቻለው ከህዝብ የሚያገኛቸውን አቅሞች ሁሉ በመንፈግ፣ በማሳጣት ብቻ ነው። እምቢኝ እምቢኝ ለአፋኞች! እምቢኝ ለግፈኞች! እምቢኝ ለዘረኛ ጠባቦች! ማናቸውንም ትብብርህ ፣ ገንዘብ፣ እውቅና መንፈግ፣ ማቆም ስንችል ነው።
ድብቅ ፋሽታዊነቱን በየግዜው እየተገለጠ የመጣው የአብይ አህመድ አገዛዝን የሚቀጡ የሰላማዊ እምቢተኝነት ስልቶች በጋራ ከታገልነው እናስገድደዋለን፣ የአንድ አገዛዝ ጥንካሬ የሚመነጨው ከህዝብ አለመደራጀትና ፣ አለመናበብ፣ ለመብቱ ለነጻነቱ በጋራ መታገል አለመቻል ብቻ ነው።
All reactions:22