Mesfin Mamo Tessema 

 · * የዓለም ዓቀፍ የእናቶች ቀን አመጣጥና አከባበር ምን ይመስላል ?

ዓለም ዓቀፍ የእናቶች ቀን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከ1914ዓ.ም ጀምሮ በይፋ እየተከበረ የሚገኝ የእናቶች መታሰቢያ በዓል ነው። ይህ ቀን በኢትዮጵያም ይከበራል። ለመህኑ የእናቶች ቀን እንዴት መከበር ጀመረ? ታሪካዊ ዳራውስ ምን ይመስላል?

ቅድመ ታሪክ

የእናቶች ቀን ታሪክ ወደ ጥንት ግሪኮችና ሮማዊያን ወደ ኋላ ይወስደናል። ጥንታዊ ግሪኮችና ሮማዊያን rhea & Cybele ለተባሉ እናት አማልክቶች የምስጋና ፌስቲቫል ያዘጋጁ ነበር። በቀደምት ክርስቲያን ታሪክም እናት ሰንበት(mothering sunday) የሚባል ፌስቲቫል እንደነበር ታሪክ ያወሳል። በዩናይትድ ኪንግደም(united kingdom) እና በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ይከበር የነበረው ይህ ቀን በዐቢይ ጾም አራተኛው እሁድ የሚውል ሲሆን ቀኑም አማኞች በአቅራቢያቸው ወዳለች ወደ እናት ቤተክርስትያን ለተለየ አገልግሎት የሚሰባሰቡበት ነበር። በጊዜ ሂደት ይህ ሀይማኖታዊ ስረዓት ከቤተክርስቲያን እየተነጠለ የመጣ ሲሆን በዚህ ቀን ልጆች ለእናቶቻቸው አበባና ስጦታ ወደሚያበረክቱበት ልምድ እየተቀየረ ሊሄድ ችሏል። ይህም ልማድ ከግዜ ብዛት ቀስ በቀስ በአሜሪካኖቹ የእናቶች ቀን አከባበር ባህል በ1930ዎቹ እና 40ዎቹ እየተዋጠና እየደበዘዘ ሌላ መልክ መያዝ ጀመረ።

መስራች እናቶች (founding mothers)

በአሜሪካ በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከእርስ በእርስ ጦርነቱ(civil war) ቀደም ብሎ Ann Reeves Jarvis የተባለች አንዲት የምዕራብ ቨርጂኒያ(west virginia) ሴት የእናቶች ቀን ክለብ በማቋቋም የአከባቢውን እናቶች እንዴት ልጆቻቸውን መንከባከብ እንዳለባቸው ማስተማር ጀመረች። ብኋላም Jarvis በ1868ዓ.ም የእናቶች ወዳጅነት ቀንን በማደራጀት የአሜሪካንን ውህደት እውን ለማድረግ በነበረው ጥረት ውስጥ እናቶች ጎራ ለይተው የሚዋጉትን ወታደሮች በማስታረቅ ትልቁን ሚና እንዲጫወቱ ረድታለች።

ሌላዋ የእናቶች ቀን መስራች እናት ለአሜሪካን ሴቶች የመምረጥ መብት በመታገል የምትታወቀው Julia ward Howe ናት። በ1870ዓ.ም Howe የእናቶች ቀን አዋጅን ይፋ አደረገች። በአዋጁም የዓለም እናቶች ለዓለም ሰላም እንዲተባበሩ ጥሪዋን አስተላልፋ ነበር። በዚህም መሰረት Howe የእናቶች የሰላም ቀን በየዓመቱ june,2 እንዲከበር በ1873ዓ.ም. ዘመቻ አድርጋም ነበር። በእናቶች ቀን መስራች እናትነት(founding mothers) ታሪክ ውስጥ ከሚጠቀሱት ባለታሪኮች Juliet Calhoun Blakely, Mary Towels Sasseen እና Frank Heringን የመሳሰሉት ይገኙበታል

።አና ጃርቪስ(Anna Jarvis)

የአባት እዳ ለልጅ እንደሚባለው Ann Reeves Jarvis የእናቶችን ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲከበር የማድረግ ህልሟን ለልጇ Anna Jarvis አውርሳት ሞተች። የእናቷ ልጅ የሆነችው Anna jarvisም የበ1908ዓ.ም. የእናቶች ቀን በwest virginia ደረጃ እንዲከበር አደረገች። ከዛም በ1912ዓ.ም ብዙ የአሜሪካ ግዛቶችና ከተሞች ቀስ በቀስ የ west virginiaን ፈለግ መከተል ጀመሩ። በዚህ ብቻ ያልረካችው Anna Jarvis ጥረቷን አጠናክራ በመቀጠል በ1914ዓ.ም. ፕሬዝዳንት Woodrow Wilson በየዓመቱ በግንቦት ወር የሚውለው ሁለተኛ እሁድ በብሄራዊ ደረጃ የእናቶች ቀን መታሰቢያ እንዲሆን የሚያጸድቀውን ውሳኔ አስፈርማ የእናቷ አጽም በሰላም እንዲያርፍ አድርጋለች።

Anna Jarvis በመጀመሪያ ቀኑ ተከብሮ እንዲውል የምታስብ የነበረው በቤተሰብ ደረጃ ልጆች እናቶቻቸውን በመጎብኘት አሊያም በቤተክርስቲያን ነበር። ይሁንና ይህ ምኞቷ ሳይሆን ቀርቶ ኋላ ላይ የቀኑን አከባበር የንግዱ ስረዓት ስለበረዘባት መበሳጨት ጀመረች። በተለይም የአበባ እና የስጦታ ካርድ ነጋዴዎች እለቱን ለገባያ ጥቅማቸው በሚመች መልኩ እንዲከበር እያደረጉት እንደሆነ ስትረዳ ይበልጡን ተናደደች። የቀኑ አከባበር እሷ ካለመችው መንገድ እያፈነገጠ ሲመጣ ተቃውሞዋን ማሰማት የጀመረችው Anna Jarvis ሁኔታው ሲባባስ ቀኑ ከአሜሪካ ካላንደር ላይ እንዲሰረዝ በዘመቻ እስከመጠየቅም ደርሳ ነበር።

የእናቶች ቀን በዓለም ሀገራትበተለያዩ ሀገራት

የእናቶች ቀን አከባበር የተለያየ ባህልና ለዛ አለው። ለምሳሌ በታይላንድ የእናቶች ቀን ንግስቲቱ sirikit በተወለደችበት በነሐሴ ወር ነው የሚከበረው። በአሜሪካ የእናቶች ቀን Anna Jarvis እንደፈራችው ትልቁ የካርድና የአበባ ሸመታ ቀን ሆኖ ለእናቶች አባባና ልዩ ልዩ ስጦታዎችን በማበርከት ይከበራል። ቀኑን በተለያየ ዘመናት የሴቶች መብት መከበረን የታገሉ ስመጥሮች ለእኩልነት ጥሪ ዘመቻቸው ተጠቅመውበታል።

በሀገራችን ኢትዮጵያም እራሱን የቻለ እናቶች የሚከበሩበት ባህል አለ። አንትሮሽት ይባላል። አንትሮሽትን በሰፊው እንመለስበታለን።

ክብር ለእናቶቻችን !!![