ፍርድ ቤቱን የተካው የአገዛዙ የሚዲያ ቅሌት… !
የዐቢይ አህመድ አገዛዝ በሚዲያው ላይ ለመግለጽ የሚከብድ ግፍ እየፈፀመ ይገኛል።
ከእነዚህ የአገዛዙ ነውረኝነት ከጥቂቱ በትንሹ ማሳያዎቸ እንግለጽ፦

ባለፉት አንድ ወር የታሰሩ የአማራ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ ፋኖዎች እና የማህበረሰብ አንቂዎችን ወንጀለኛ መሆናቸውን የሚያሳይ ፕሮፓጋንዳ እንዲሰራ በዐቢይ አህመድ ቀጥተኛ ትዕዛዝ፣ በመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ዋና አስፈጻሚነት አንድ ቡድን ተቋቁሟል። የዚህ ቡድን መሪም የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት ካሳ ስትሆን በሥሯም ከፋና፣ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ ከዋልታ እና ከኢትዮጲያ ዜና አገልግሎት ቋሚ ዘጋቢዎችን አስመድባለች።
የአገዛዙን ነውረኝነት ለማስረዳት እንዲያግዘን በምሳሌ እንመልከተው። አብዛኛውን የችሎት ዘገባው የምትሰራው ታሪክ አዱኛ የምትባል ጋዜጠኛ ስትሆን ከፋና ከለቀቀች በኋላ የችሎት ዘገባ ላይ ባላት የረጅም ዓመት ልምድ ምክንያት ፋና በፍሪላንስ የችሎት ዘገባን እንድትሰራለት አግባብቶ እንደገና የመለሳት የችሎት ዘጋቢ ነች። አሁን ላይ በፍሪላንስነት እየሰራች ሲሆን የችሎት ዜናውን መጀመሪያ በቀጥታ ወደ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ እንድትልክ የምትገደድ ሲሆን ሰላማዊት ካሳም የአገዛዙ አድራጊ እና ፈጣሪ አቢይ አህመድ በሚፈልገው መልኩ እንደ አዲስ ጽፋ ለፋና ኃላፊዎች ይሄ ይዘገብ ብላ ትልከዋለች።
በዚህም ከፋና የተመደበችው ታራክ አዱኛ የችሎት ክርክሩን የግራ ቀኝ ሐሳብ አካታ ብትልክም የአብይ አህመድ ቀኝ እጅ እና አማራን ወክላ ስልጣን ላይ የተቀመጠችው ሰላማዊት ካሳ የፖሊስና ዳኞችን ሐሳብ ብቻ አስቀርታ የተጠርጣሪዎቹን እና የጠበቆቻቸውን ሐሳብ ሙሉ በሙሉ አስወጥታ ለሕዝብ እንዲደርስ እያደረገች ትገኛለች።
መታወቅ ያለበት እውነት፦ ፍርድ በሚዲያ እየተሠጠ ነው። በሕግ የተያዘ ጉዳይ በሚዲያ ፕሮፓጋንዳ እና በፍርድ ቤት ላይ ጫና እየተፈጠረ እየተፈረደባቸው እና እየተሰቃዩ ነው።
ብያኔና ውሳኔው በሚዲያ መሆኑ ገሃድ ወጥቷል፤ የብሮድካስት አዋጁ እንደሚከለክል ሕጉን ቢያውቁትም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንን ከመጤፍ አልቆጠሩትም (ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም የተጠርጣሪዎች እና የጠበቆች ሀሳብ አለመካተቱን እያወቀ ባላዬ አልፎታል።) ይህ ተቋም ተጠሪነቱ ለሕ/ተ/ም/ቤት ቢሆንም ስለጉዳዩ ያነሳ እንደራሴ አልተመለከትነም።
በነገራችን ላይ መሰመር ያለበት እውነት፤ የሰዎችን በሕግ ብቻ የመዳኘት መብት ይጥሳል። ቋሚ ኮሚቴው (ካለ) ማጣሪያ ማድረግ አለበት። ሚዲያዎቹ የአገዛዙ ልዩ መሣሪያ፣ ሀሳብን በነጻነት ከመግለጽ ይልቅ ፈራጅ እና አስፈራጅ ሁነዋል፤ በአናቱም በዓለም አቀፍ ሕግ የተደነጉ የሰብዓዊ እና የዲሞክራሲያዊ የመብት አንቀጿችን ደፍጥጠዋል።
ድል ለአማራ !!
