
ከ 9 ሰአት በፊት
በሩሲያ የአሜሪካ ኤምባሲ የቀድሞ ሠራተኛ የነበሩ አሜሪካዊ ሞስኮ ውስጥ መታገታቸው ተጠቆመ።
የሩሲያ መንግሥት የሚያስተዳድረው ታስ የተባለው መገናኛ ብዙኃን ባወጣው ዘገባ መሠረት የቀድሞው የአሜሪካ ኤምባሲ ሠራተኛው ሞስኮ በሚገኝ የዕገታ ማዕከል ውስጥ “በመመሳጠር” ክስ ታግተዋል።
ሮበርት ሾኖቭ የተባሉት ግለሰብ በሩሲያ ፌደራል የደኅንነት ኃይል ታስረው “በጥብቅ ቁጥጥር ሥር” ናቸው ተብሏል።
እስከ ስምንት ዓመት የሚደርስ እስራት እንደሚጠብቃቸው ተገልጿል።
ቢቢሲ በሩሲያ የአሜሪካ ኤምባሲን ምላሽ ለማግኘት ሞክሮ ነበር።
ኤምባሲው ለሮይተርስ እንደገለጸው፣ ስለ ዘገባው መረጃ ቢኖራቸውም “በዚህ ወቅት ምንም ዝርዝር መረጃ መስጠት አንችልም” ብለዋል።
ቫልዲቮስቶክ በተባለ የወደብ ከተማ ነው ግለሰቡ የተያዙት።
የምርመራ ጥያቄ ከተጠየቁ በኋላ “በሚሥጥራዊ ሁኔታ ከውጭ አገር፣ ከዓለም አቀፍ ወይም የውጭ ተቋም ጋር በማበር” በሚል ተከሰዋል ሲል ታስ ዘግቧል።
የቀድሞው የኤምባሲ ሠራተኛው እንዲታገቱ መመሪያ የወጣው ከሦስት ወራት በፊት ነው። ለፍርድ ሂደታቸው ቀነ ቀጠሮ እንዳልተሰጠም ተገልጿል።
- በኢትዮጵያ ካሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ዲዛይን ጀርባ ያለው ወጣት አርክቴክት16 ግንቦት 2023
- ‘ዘ ዊኬንድ’ መጠሪያውን ወደ ትውልድ ስሙ አቤል ተስፋዬ ቀየረከ 9 ሰአት በፊት
- ዩክሬን ለወራት ስትዘጋጅ እና ስትታጠቅበት የቆየችው መልሶ ማጥቃት ምን ሊቀይር ይችላል?16 ግንቦት 2023
አሁን የሚገኙት በሞስኮው ሌፎርቶቭ እስር ቤት ሲሆን፣ ይህ እስር ቤት ቀድሞ ኬጂቢ የሚጠቀምበት ነበር።
ለዋል ስትሪት ጆርናል ሲሠራ የታገተው አሜሪካዊው ጋዜጠኛ ኤቫን ገርሻኮቪች በስለላ ተከሶ እዛው እስር ቤት ነው የሚገኘው።
የቀድሞው የአሜሪካ ባሕር ኃይል ፖል ኤልንም እዛው እስር ቤት የሚገኝ ሲሆን እአአ በ2020 የ16 ዓመታት እስር ተፈርዶበታል።
በ2018 በስለላ ነበር የተከሰው።
አሜሪካ ሁለቱም ዜጎቿ ላይ የቀረበው ክስ መሠረተ ቢስ እንደሆነ ትገልጻለች።
